Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ምሳሌ 19:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 በንግግሩ ከሚቀላምድ ሞኝ ሰው ይልቅ በቅንነት የሚኖር ድኻ ሰው ይሻላል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ንግግሩ ጠማማ ከሆነ ሞኝ ሰው ይልቅ፣ ያለ ነውር የሚሄድ ድኻ ሰው ይሻላል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 በከንፈሩ ከሚወሳልት ሰነፍ ይልቅ ያለ ነውር የሚሄድ ድሀ ይሻላል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 በከንፈሩ ከሚወሳልት አላዋቂ ይልቅ፥ ያለ ነውር የሚሄድ ድሃ ይሻላል።

参见章节 复制




ምሳሌ 19:1
16 交叉引用  

እኔ በበኩሌ ነቀፋ የሌለበት ሕይወት እኖራለሁ፤ ምሕረትን አድርግልኝ፤ አድነኝም!


ደግ ሰው ሁልጊዜ በልግሥና ይሰጣል፤ እንዲሁም ያበድራል፤ ልጆቹም የተባረኩ ይሆናሉ።


እውነተኛ ሰው ወዳጁን በመምከር ወደ ቅን መንገድ ይመራዋል፤ የዐመፀኞች መንገድ ግን ከእውነት የሚያርቅ ነው።


አካሄዱ ቀጥተኛ የሆነ ሰው እግዚአብሔርን ይፈራል፤ መንገዱ ጠማማ የሆነ ሰው ግን እግዚአብሔርን አይፈራም።


ሀብታም ሆኖ በሁከት ከመኖር ድኻ ሆኖ እግዚአብሔርን በማክበር መኖር ይሻላል።


ፍትሕን በማጓደል ከሚገኝ ብዙ ሀብት ይልቅ በእውነት የሚገኝ ጥቂት ነገር ይሻላል።


ከሰው የሚፈለገው ታማኝነት ነው፤ ሐሰተኛ ከመሆን ይልቅ ድኻ መሆን ይሻላል።


ጻድቅ ሰው በቅንነት ይኖራል፤ የእርሱ ልጆችም የተባረኩ ናቸው።


ሀብታም ሆኖ አታላይ ከመሆን ይልቅ ድኻ ሆኖ ታማኝ መሆን ይሻላል።


ክፉ ንግግር ከአፍህ አይውጣ፤ ሐሰትንና ማታለልን ከአንተ አርቃቸው።


እጆቻችሁ በደም፥ ጣቶቻችሁም በበደል ተበክለዋል፤ አፋችሁ ውሸትን ይናገራል፤ በአንደበቶቻችሁም ታጒተመትማላችሁ።


ሰው የዓለሙን ሁሉ ሀብት ቢያገኝ፥ ነፍሱን ግን ቢያጠፋ፥ ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ዋጋ ሊከፍል ይችላል?


እባክሽን ይህን ጉዳይ አስቢበትና ማድረግ ስለሚገባሽ ነገር ወስኚ፤ አለበለዚያ ለጌታችንና ለቤተሰቡ ሁሉ አደገኛ ጥፋት ይሆናል፤ እርሱ እንደ ሆነ የማንንም ምክር የማይሰማ ደረቅ ሰው ነው!”


የናባልን ጉዳይ ከቁም ነገር አታግባው! እርሱ ልክ እንድ አስሙ አጠራር ሞኝ ነው! ጌታዬ፥ የአንተ አገልጋዮች በመጡ ጊዜ እኔ በዚያ አልነበርኩም፤


跟着我们:

广告


广告