Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ምሳሌ 17:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ሞኝ መቶ ጊዜ ተገርፎ ከሚማረው ይልቅ አስተዋይ ሰው ከአንድ ጊዜ በማይበልጥ ተግሣጽ የሚማረው ይበልጣል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 መቶ ግርፋት ሞኝን ከሚሰማው ይልቅ፣ ተግሣጽ ለአስተዋይ ጠልቆ ይሰማል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 መቶ ግርፋት በሰነፍ ጠልቆ ከሚገባ ይልቅ ተግሣጽ በአስተዋይ ሰው ጠልቆ ወደ ልቡ ይገባል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ትምክሕት የአስተዋይ ሰው ልቡናን ያሳዝነዋል፥ አላዋቂ ግን ተገርፎ ግርፋቱ አይታወቀውም፥

参见章节 复制




ምሳሌ 17:10
10 交叉引用  

ደግ ሰው በቅንነት መንፈስ ሊቀጣኝና ሊገሥጸኝ ይችላል፤ ከክፉ ሰዎች ግን ክብርን እንኳ አልቀበልም፤ ዘወትርም ክፉ ሥራቸውን በመቃወም እጸልያለሁ።


ብልኅ ልጅ የአባቱን ምክር ይቀበላል፤ ፌዘኛ ግን ተግሣጽን አይሰማም።


ሞኝ የአባቱን ምክር ይንቃል፤ ተግሣጽን የሚቀበል ግን አስተዋይ ነው።


ክፉ ሰው ሁልጊዜ ዐመፀኛ ነው፤ ስለዚህ ምሕረት የሌለው መልእክተኛ ይላክበታል።


የበደለን ሰው ይቅር የሚል ወዳጅነትን ያጸናል፤ በደልን መላልሶ የሚናገር ሰው ግን የቅርብ ወዳጆቹን ያጣል።


ፌዘኛ ብትቀጣው አላዋቂው ብልኅ ይሆናል፤ አስተዋይ ሰው ብትገሥጸው የበለጠ ዕውቀትን ይጨምራል።


እህል በሙቀጫ ውስጥ በዘነዘና እንደሚወቀጥ ሞኝንም ለመሞት እስኪቃረብ ድረስ ብትመታው እንኳ ሞኝነቱን ከእርሱ ማስወገድ አትችልም።


አንድን አገልጋይ በቃል በመገሠጽ ብቻ ለማረም አይቻልም፤ የምትለው ነገር ቢገባው እንኳ አይታዘዝም።


እኔ የምወዳቸውን ሁሉ እገሥጻቸዋለሁ፤ እቀጣቸዋለሁም፤ ስለዚህ ትጋ፤ ንስሓም ግባ፤


跟着我们:

广告


广告