Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ምሳሌ 16:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ተንኰለኛ ሰው ጠብን ይዘራል፤ ሐሜተኛም የቅርብ ወዳጆችን እንዲለያዩ ያደርጋል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 ጠማማ ሰው ጠብን ይዘራል፤ ሐሜተኛም የቅርብ ወዳጆችን ይለያያል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 ጠማማ ሰው ጥልን ይዘራል፥ ጆሮ ጠቢ ሰው የተማመኑትን ወዳጆች ይለያያል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 ጠማማ ሰው ክፋትን ይዘራል፥ የሐሰት መብራት ክፉዎችን ታቃጥላቸዋለች፥ ወዳጆችንም ትለያለች።

参见章节 复制




ምሳሌ 16:28
18 交叉引用  

ቊጣ ጭቅጭቅን ያነሣሣል፤ ትዕግሥት ግን ጠብን ያበርዳል።


ወንበዴ ክፉ ነገርን ያቅዳል ንግግሩም እንደ እሳት ያቃጥላል።


ዐመፀኛ ሰውን ያታልላል፤ ወደ ጥፋትም ይመራል።


ወዳጅ ምን ጊዜም ቢሆን ወዳጁን ይወዳል፤ ወንድም የሚወለደው የወንድሙን ችግር ለመካፈል ነው።


የበደለን ሰው ይቅር የሚል ወዳጅነትን ያጸናል፤ በደልን መላልሶ የሚናገር ሰው ግን የቅርብ ወዳጆቹን ያጣል።


የሞኝ ንግግር ጠብን ያነሣሣል፤ ልፍለፋውም በትርን ይጋብዛል።


የሐሜተኛ ሰው ቃል እንደ ጣፋጭ ምግብ ደስ እያሰኘ እስከ ውስጥ ሰውነት ድረስ ይወርዳል።


ቊጡ ሰው ጠብን ያነሣሣል፤ ግልፍተኛም ብዙ በደልን ይፈጽማል።


ወተት ቢናጥ ቅቤ ያስገኛል፤ የሰው አፍንጫ ቢጠመዘዝ ይደማል፤ ቊጣ ቢነሣሣ ጠብን ያመጣል።


በጠማማ አእምሮው ዘወትር ክፉ ነገርን ለማድረግ ያቅዳል፤ ሁልጊዜ ጠብን ይዘራል።


በውሸት ላይ ውሸት እየጨመረ የሚናገር ምስክር፥ በወዳጆች መካከል ጠብ የሚያነሣሣ ሰው።


ስለዚህ በበደል፥ በክፋት፥ በሥሥት፥ በተንኰል፥ በምቀኝነት፥ በነፍሰገዳይነት፥ በጥል፥ በአታላይነት፥ በክፉ ምኞት ሁሉ የተሞሉ፥ እንዲሁም ሐሜተኞች ናቸው፤


እኔ ወደዚያ በምመጣበት ጊዜ ምናልባት ልትሆኑ እንደምፈልገው ሳትሆኑ፥ እኔም እናንተ እንደምትፈልጉት ሳልሆን እንገናኝ ይሆናል ብዬ እፈራለሁ፤ እንዲሁም በእናንተ ዘንድ ጥል፥ ቅናት፥ ቊጣ፥ ራስ ወዳድነት፥ የሰው ስም ማጥፋት፥ ሐሜት፥ ትዕቢትና ሁከት ይኖሩ ይሆናል ብዬ እፈራለሁ።


“እኔ አንተን ጒዳት እንደማደርስብህ አስመስለው የሚነግሩህን ሰዎች ቃል ስለምን ትሰማለህ?


跟着我们:

广告


广告