Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ምሳሌ 15:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 እግዚአብሔር በየቦታው የሚደረገውን ነገር ሁሉ ያያል። መልካምም ሆነ ክፉ ድርጊትን ይመለከታል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 የእግዚአብሔር ዐይኖች በሁሉም ስፍራ ናቸው፤ ክፉዎችንም ደጎችንም ነቅተው ይመለከታሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 የጌታ ዐይኖች በስፍራ ሁሉ ናቸው፥ ክፉዎችንና ደጎችን ይመለከታሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 የእግዚአብሔር ዐይኖች በሁሉ ቦታ ናቸው፤ ክፉዎችንና ደጎችንም ይመለከታሉ።

参见章节 复制




ምሳሌ 15:3
13 交叉引用  

እግዚአብሔር መላውን ዓለም አተኲሮ በመመልከት፥ በሙሉ ልባቸው በእርሱ ለሚተማመኑት ሁሉ ብርታትን ይሰጣቸዋል፤ እንግዲህ አንተ የሞኝነት ሥራ ስለ ፈጸምክ ከእንግዲህ ወዲህ ጦርነት አይለይህም፤”


እግዚአብሔር በሰላም እንዲኖሩ ቢፈቅድላቸውም እንኳ የሚሄዱበትን መንገድ ሁሉ አተኲሮ ይመለከታል።


እርሱም የምድርን ዳርቻ ሁሉ ይመለከታል፤ ከሰማይ በታች ያለውን ሁሉ ያያል።


እግዚአብሔር የማደርገውን ሁሉ አያይምን? እርምጃዎቼንስ አይቈጣጠርምን?


እግዚአብሔር ከሰማይ ሆኖ ይመለከታል፤ የሰውንም ዘር ሁሉ ያያል፤


ለስላሳ አነጋገር ሕይወትን ይሰጣል። ተንኰል የተሞላበት አነጋገር ግን መንፈስን ይሰብራል።


እግዚአብሔር ሰው የሚያደርገውን ሁሉ ያያል፤ የሚሄድበትንም መንገድ ሁሉ ይመለከታል።


የሚያደርጉትን ሁሉ አያለሁ፤ ከእኔ የሚሰወር ምንም ነገር የለም፤ ኃጢአታቸው ሁሉ በፊቴ የተገለጠ ነው።


እኔ ሰማይንና ምድርን የሞላሁ አይደለሁምን? ሰው በስውር ቦታ ቢሸሸግ እኔ አላየውምን?


ዓላማህ ታላቅ ነው፤ ሥራህም ኀያል ነው፤ ሕዝቦች የሚያደርጉትን ነገር ሁሉ ታያለህ፤ ለእያንዳንዱም ሰው እንደአካሄዱና እንደየሥራው ዋጋውን ትከፍላለህ።


ትንሽ ነገር የሚደረግበትን ቀን የናቀ ቱምቢውን በዘሩባቤል እጅ ሲያይ ይደሰታል፤ እነዚህ ሰባቱ መቅረዞች ዓለምን የሚያካልሉ የእግዚአብሔር ዐይኖች ናቸው።”


ከእግዚአብሔር ፊት የሚሰወር ምንም ፍጥረት የለም፤ በእርሱ ዐይን ፊት ሁሉ ነገር ግልጥና ዕርቃኑን ሆኖ የሚታይ ነው፤ እኛም መልስ መስጠት የሚገባን በእርሱ ፊት ነው።


跟着我们:

广告


广告