Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ምሳሌ 15:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ማስተዋል የጐደላቸው ሰዎች በሞኝነታቸው ይደሰታሉ፤ ብልኆች ግን ትክክል የሆነውን ነገር ያደርጋሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ልበ ቢስ ሰው ቂልነት ያስደስተዋል፤ አስተዋይ ሰው ግን ቀጥተኛውን መንገድ ይከተላል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ልብ ለሌለው ሰው ስንፍና ደስታ ናት፥ አስተዋይ ግን አካሄዱን ያቀናል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 የአላዋቂ ሰው መንገዶች ጠማሞች ናቸው፤ ብልህ ሰው ግን አቅንቶ ይሄዳል።

参见章节 复制




ምሳሌ 15:21
13 交叉引用  

“በዚያን ጊዜ ሰውን ‘እነሆ፥ ጥበብ ማለት እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ ማስተዋልም ማለት ከክፋት መራቅ ነው’ ብሎታል።”


እግዚአብሔርን መፍራት የጥበብ መጀመሪያ ነው፤ ትእዛዙን የሚፈጽሙትን ሁሉ አስተዋዮች ያደርጋቸዋል፤ እግዚአብሔር ለዘለዓለም የተመሰገነ ይሁን!


ስሕተት በማድረግ መደሰት ሞኝነት ነው፤ በአእምሮ የበሰሉ ሰዎች ደስ የሚላቸው ጥበብን በማግኘት ነው።


በንቀት ተናግሮ ሰውን የሚያዋርድ፥ ማስተዋል የጐደለው ነው፤ አስተዋይ ሰው ግን ዝም ይላል።


ብልኆች እግዚአብሔርን ስለሚፈሩ ከክፉ ነገር ለመራቅ ይጠነቀቃሉ፤ ሞኞች ግን ከአደጋ የማይጠነቀቁ ችኲሎች ናቸው።


የብልኅ ሰው ጥበብ መንገዱን እንዳይስት ያደርገዋል። ሞኝን ሰው ግን ሞኝነቱ መንገዱን እንዲስት ያደርገዋል።


ሞኞች ኃጢአት ሲሠሩ በመጸጸት ፈንታ ያፌዛሉ፤ ደጋግ ሰዎች ግን ኃጢአታቸው ይቅር እንዲባልላቸው ይፈልጋሉ።


መልካም ምክርን ብትቀበል ሁሉ ነገር ይሳካልሃል፤ ምክርን ባትቀበል ግን ምንም ነገር አይሳካልህም።


አመለካከትህ ቀጥተኛ ይሁን፤ ግራና ቀኝ ሳትል ወደፊት ተመልከት።


እግሮችህ በቀና መንገድ ላይ ይራመዱ። መንገድህም ሁሉ ይቃናልሃል።


እንግዲህ እንዴት እንደምትኖሩ በጥንቃቄ አስተውሉ፤ እንደ ጥበበኞች እንጂ እንደ ሞኞች አትኑሩ።


ከእናንተ መካከል ጥበበኛና አስተዋይ ሰው ማን ነው? በጥበብና በትሕትና የፈጸመውን ሥራ በመልካም አኗኗሩ ያሳይ።


跟着我们:

广告


广告