Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ምሳሌ 14:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ጥበበኛ ሴት ቤትዋን በሥነ ሥርዓት ታስተዳድራለች፤ ሞኝ ሴት ግን በገዛ እጅዋ ታፈርሰዋለች።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ጠቢብ ሴት ቤቷን ትሠራለች፤ ቂል ሴት ግን በገዛ እጇ ታፈርሰዋለች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ብልሃተኛ ሴት ቤትዋን ትሠራለች፥ ሰነፍ ሴት ግን በእጅዋ ታፈርሰዋለች።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ብልሆች ሴቶች ቤቶችን ይሠራሉ፤ ሰነፎች ሴቶች ግን በእጃቸው ያፈርሳሉ።

参见章节 复制




ምሳሌ 14:1
10 交叉引用  

አክዓብ፥ ንጉሥ ኢዮርብዓም የሠራውን ኃጢአት እንደ ቀላል ነገር አድርጎ በመቊጠር እርሱም ራሱ ያንኑ ኃጢአት ሠራ፤ ከዚህም ሁሉ አልፎ የሲዶና ንጉሥ የኤትበዓል ልጅ የሆነችውን አረማዊቷን ኤልዛቤልን አገባ፤ ባዓል ተብሎ የሚጠራውንም ጣዖት አመለከ፤ ሰገደለትም፤


የንጉሥ አካዝያስ እናት ዐታልያ የልጅዋን መገደል እንደ ሰማች ወዲያውኑ የይሁዳ ንጉሣውያን ቤተሰብ አባላት በሙሉ እንዲገደሉ ትእዛዝ ሰጠች።


ሞኝ ልጅ አባቱን ወደ ጥፋት ያደርሳል፤ ጨቅጫቃ ሚስትም እንደማያቋርጥ ዝናብ አሰልቺ ናት።


ከጨቅጫቃና ከነዝናዛ ሚስት ጋር አብሮ ከመኖር በምድረ በዳ መኖር ይሻላል።


ከጨቅጫቃ ሚስት ጋር በአንድ ቤት ከመኖር ይልቅ በጣራ ማእዘን ላይ መኖር ይሻላል።


በአደባባይ ተቀምጠው የነበሩት ሽማግሌዎችና ሌሎችም ሰዎች እንዲህ አሉ፥ “አዎ፥ እኛ ለዚህ ነገር ምስክሮች ነን፤ እግዚአብሔር ይህችን ሚስትህን ብዙ ልጆችን በመውለድ የያዕቆብን ቤት እንደ መሠረቱት እንደ ራሔልና እንደ ልያ ያድርግልህ፤ እግዚአብሔር በኤፍራታ ያበልጽግህ፤ በቤተልሔምም ዝነኛ ያድርግህ፤


跟着我们:

广告


广告