Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ምሳሌ 12:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ያለ ጥንቃቄ የተነገረ ቃል እንደ ሰይፍ ያቈስላል፤ በጥበብ የተነገረ ቃል ግን ይፈውሳል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ግድ የለሽ ቃል እንደ ሰይፍ ይወጋል፤ የጠቢብ አንደበት ግን ፈውስን ያመጣል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 እንደሚዋጋ ሰይፍ የሚለፈልፍ ሰው አለ፥ የጠቢባን ምላስ ግን ጤና ነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 በሐሰት የሚመሰክሩ በሰይፍ ይገድላሉ፤ በአፋቸው ሰይፍ አለና። የጠቢባን ምላስ ግን የቈሰለውን ይፈውሳል።

参见章节 复制




ምሳሌ 12:18
17 交叉引用  

አንተ ተንኰለኛ ጥፋትህን ታሤራለህ፤ አንደበትህ እንደ ተሳለ ምላጭ ነው።


ጥርሶቻቸው እንደ ጦሮችና ቀስቶች፥ ምላሶቻቸው እንደ ተሳሉ ሰይፎች በሆኑ፥ ሰውን በሚበሉ አንበሶች መካከል ተደፍቼ ተኝቼአለሁ።


አምላክ ሆይ! ከሰማያት ሁሉ በላይ ከፍ ከፍ በል፤ ክብርህም በምድር ሁሉ ላይ ይሁን።


ከአፋቸው የሚወጣውን ተመልከት፤ ምላሳቸው እንደ ተሳለ ሰይፍ ነው፤ ነገር ግን ማንም የሚሰማቸው አይመስላቸውም።


እነርሱ ምላሳቸውን እንደ ሰይፍ ይስላሉ፤ እጅግ የከፋ ቃላትን እንደ ፍላጻ አነጣጥረው ይወረውራሉ።


እውነትን የሚናገር ሁሉ የታመነ ምስክርነትን ይሰጣል፤ ሐሰተኛ ምስክር ግን ሰውን ያታልላል።


ክፉ መልእክተኛ ችግርን ያመጣል፤ ታማኝ መልእክተኛ ግን ሰላምን ያስገኛል።


ለስላሳ አነጋገር ሕይወትን ይሰጣል። ተንኰል የተሞላበት አነጋገር ግን መንፈስን ይሰብራል።


ዕውቀት የሚስፋፋው በብልኆች እንጂ በሞኞች አይደለም።


መልካም ንግግር እንደ ማር. ወለላ ይጣፍጣል፤ ለሰውነትም ፈውስ የሚሰጥ ነው።


በባልንጀራው ላይ በሐሰት የሚመሰክር ሰው የሰይፍ፥ የዱላና የተሳለ ፍላጻ ያኽል ሊጐዳው ይችላል።


እነርሱም ለሚያስተውሉአቸው ሕይወትን፥ ለመላ ሰውነትም ጤንነትን ይሰጣሉ።


በሕዝቡ መካከል ያሉ ጠቢባን ሕዝቡን በማስተማር ዕውቀት እንዲያገኝ ያደርጋሉ፤ ነገር ግን ለጥቂት ጊዜ ለእሳት ቃጠሎና ለሰይፍ ስለት የተጋለጡ ይሆናሉ፤ ሀብታቸውንም ተዘርፈው ይታሰራሉ።


በቀኝ እጁ ሰባት ኮከቦችን ይዞ ነበር፤ በሁለት በኩል ስለት ያለው ሰይፍ ከአፉ ይወጣ ነበር፤ ፊቱም በሙሉ ድምቀቱ እንደሚያበራ ፀሐይ ነበረ።


ይህ ወንዝ በከተማይቱ ዋና መንገድ መካከል ሰንጥቆ ያልፋል፤ በወንዙ ግራና ቀኝ በየወሩ እያፈራ በዓመት ዐሥራ ሁለት ጊዜ ፍሬ የሚሰጥ የሕይወት ዛፍ ነበረ፤ የዛፉም ቅጠሎች ሕዝቦችን ለመፈወስ ያገለግላሉ።


跟着我们:

广告


广告