Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ምሳሌ 11:29 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 በቤተ ሰቡ ላይ ሁከት የሚያመጣ ሰው ምንም የሚያተርፈው ጥቅም የለም፤ ሞኞች ዘወትር ለጠቢባን አገልጋዮች ይሆናሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 ቤተ ሰቡን የሚያውክ ሰው ነፋስን ይወርሳል፤ ቂልም ሰው የጠቢብ ባሪያ ይሆናል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 ቤቱን የሚያውክ ሰው ነፋስን ይወርሳል፥ አላዋቂም ለጠቢብ ተገዥ ይሆናል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 ቤቱን የማያውቅ ሰው ነፋስን ይወርሳል፥ ሰነፍም ለጠቢብ ተገዥ ይሆናል።

参见章节 复制




ምሳሌ 11:29
10 交叉引用  

ያዕቆብ ስምዖንንና ሌዊን እንዲህ አላቸው፤ “በእኔ ላይ ከባድ ችግር አመጣችሁብኝ፤ እነሆ በዚህ ድርጊት የተነሣ በዚህች ምድር የሚኖሩ ከነዓናውያንና ፈሪዛውያን ይጠሉኛል፤ እኛ በቊጥር አነስተኞች ነን፤ እነርሱ ተባብረው ቢያጠቁን እኔና ቤተሰቤ እንጠፋለን።”


ክፉዎች በደጋግ ሰዎች ፊት ይንበረከካሉ፤ ኃጢአተኞች በጻድቃን ደጅ ያጐነብሳሉ።


በማጭበርበር ትርፍ ለማግኘት ብትሞክር ቤተሰብህን በችግር ላይ ትጥላለህ፤ ጉቦ አትቀበል፤ ለረጅም ዘመንም ትኖራለህ።


ራቁቱን እንደ ተወለደ ራቁቱን መሄዱ እጅግ የሚያሳዝን ነው፤ ድካሙ ሁሉ ነፋስን እንደ መጨበጥ ከንቱ ከሆነ ጥቅሙ ምንድን ነው?


እነርሱ ነፋስን ዘርቶ ዐውሎ ነፋስን እንደሚያጭድ ይሆናሉ፤ ዛላ የሌለው የእህል አገዳ ምግብ ሊሆን አይችልም፤ ፍሬ ቢኖረውም እንኳ የሚበሉት ባዕዳን በሆኑ ነበር።


እባክሽን ይህን ጉዳይ አስቢበትና ማድረግ ስለሚገባሽ ነገር ወስኚ፤ አለበለዚያ ለጌታችንና ለቤተሰቡ ሁሉ አደገኛ ጥፋት ይሆናል፤ እርሱ እንደ ሆነ የማንንም ምክር የማይሰማ ደረቅ ሰው ነው!”


ከዐሥር ቀኖች በኋላም እግዚአብሔር ስለ ቀሠፈው ናባል ሞተ።


跟着我们:

广告


广告