Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ምሳሌ 11:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 የደጋግ ሰዎች ምኞት ጥሩ ውጤት አለው፤ የክፉ ሰዎች ምኞት ግን ጥፋትን ያስከትላል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 የጻድቃን ምኞት ምን ጊዜም ፍጻሜው ያማረ ነው፤ የክፉዎች ተስፋ ግን በቍጣ ያከትማል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 የጻድቃን ምኞት በጎ ብቻ ነው፥ የክፉዎች ተስፋ ግን መቅሠፍት ነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 የጻድቃን ምኞት መልካም ነው፤ የኃጥኣን ተስፋ ግን ይጠፋል።

参见章节 复制




ምሳሌ 11:23
16 交叉引用  

እግዚአብሔር ሆይ! አንተ የምስኪኖችን ጸሎት ትሰማለህ፤ ልመናቸውንም አድምጠህ ታበረታታቸዋለህ።


አንተን በሙሉ ልቤ ስለምፈልግህ ትእዛዞችህን እንዳላፈርስ ጠብቀኝ።


ድንጋጌህን በመጠበቅ ታማኝ ለመሆን በብርቱ እመኛለሁ።


እግዚአብሔርን አንድ ነገር እለምነዋለሁ፤ የምለምነውም፦ በሕይወት ዘመኔ ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ የእግዚአብሔርን አስደናቂነት እንድመለከትና በቤተ መቅደሱም መጸለይ እንድችል ነው።


በእግዚአብሔር ደስ ይበልህ፤ እርሱም የልብህን ፍላጎት ሁሉ ይሰጥሃል።


የደጋግ ሰዎች ተስፋ ወደ ደስታ ይመራቸዋል፤ የክፉዎች ተስፋ ግን ከንቱ ሆኖ ይቀራል።


አንዳንድ ሰዎች በለጋሥነት ገንዘባቸውን ይበትናሉ፤ ነገር ግን ሀብታቸው እየበዛ ይሄዳል፤ ሌሎች ደግሞ ያለ ልክ ለገንዘባቸው ይሳሳሉ፤ ነገር ግን ድኽነታቸው እየበዛ ይሄዳል።


ክፉ ሰው ሲሞት ተስፋውም አብሮት ይሞታል፤ በኀይሉ መመካቱም አብሮት ይጠፋል።


የእውነተኞች ሰዎች ሐሳብ የቀና ነው፤ የክፉዎች ምክር ግን አታላይነት ነው።


ደጋግ ሰዎች የመልካም አነጋገራቸውን ዋጋ ይቀበላሉ፤ የአታላዮች ምኞት ግን የግፍ ሥራ ለመፈጸም ነው።


ፍርድህ በምድር ላይ በሚሰፍን ጊዜ የዓለም ሕዝቦች እውነትን ይማራሉ። ነፍሴ በሌሊት አንተን ትናፍቃለች፤ በውስጤም ያለው መንፈስ አንተን ትሻለች።


ነገር ግን እግዚአብሔር ሆይ! በእነርሱ ላይ መቅሠፍትን እንድታመጣ ያሳሰብኩህ ጊዜ የለም፤ የመከራ ዘመን እንዲገጥማቸውም አልተመኘሁም፤ እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ይህንና የተናገርኩትን ሁሉ ታውቃለህ።


ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ስለሚጠግቡ የተባረኩ ናቸው።


አሁን የሚቀረው ግን ወደ ፊት የሚሆነው አስፈሪ ፍርድና ተቃዋሚዎችን የሚያቃጥል አስፈሪ እሳት ነው።


跟着我们:

广告


广告