Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ምሳሌ 11:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 በእውነተኞች ሰዎች በረከት ምክንያት ከተማ እያደገች ትሄዳለች፤ የክፉ ሰዎች መጥፎ ንግግር ግን ወደ ውድቀት ያደርሳታል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 በቅኖች በረከት ከተማ ከፍ ከፍ ትላለች፤ በክፉዎች አንደበት ግን ትጠፋለች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 በቅኖች በረከት ከተማ ከፍ ከፍ ትላለች፥ በክፉዎች አፍ ግን ትገለበጣለች።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 በቅኖች በረከት ከተማ ከፍ ከፍ ትላለች፤ በኃጥኣን አፍ ግን ትገለበጣለች።

参见章节 复制




ምሳሌ 11:11
14 交叉引用  

“ስለዚህ ወደዚህ የላከኝ ራሱ እግዚአብሔር እንጂ እናንተ አይደላችሁም፤ እግዚአብሔር ለፈርዖን እንደ መካሪ አባት፥ በቤት ንብረቱ ላይ ጌታና የመላው ግብጽ አገር ገዢ አደረገኝ።


በዚያን ጊዜ ሼባዕ ተብሎ የሚጠራ ጠባዩ የተበላሸ የማይረባ አንድ ሰው በጌልገላ ይኖር ነበር፤ እርሱም ትውልዱ ከብንያም ነገድ ሲሆን አባቱ ቢክሪ ይባላል፤ ይህም ሼባዕ እምቢልታ ነፍቶ “ከዳዊት ጋር ምንም ድርሻ የለንም! ከእሴይ ልጅ ጋር ምንም ዕድል ፈንታ የለንም! የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! እያንዳንድህ ወደ ቤትህ ግባ!” ሲል ድምፁን ከፍ አድርጎ ተናገረ።


አንተም ቅን ልብ ያለህ ብትሆን እግዚአብሔር ከክፉ ሁሉ ይጠብቅሃል፤ እጆችህም ከበደል ሥራ የነጹ ቢሆኑ እግዚአብሔር ይታደግሃል።”


ለጻድቃን፥ ሁሉ ነገር ሲሳካላቸው በከተማው ውስጥ ደስታ ይሆናል። ክፉዎች ሲጠፉ ደግሞ እልልታ ይሆናል።


በንቀት ተናግሮ ሰውን የሚያዋርድ፥ ማስተዋል የጐደለው ነው፤ አስተዋይ ሰው ግን ዝም ይላል።


እውነተኛነት አንድን ሕዝብ ታላቅ ያደርገዋል፤ ኃጢአት ግን ማንኛውንም ሕዝብ ያዋርዳል።


አንድ ሕዝብ ኃጢአተኛ ሲሆን መሪዎች ይለዋወጡበታል፤ ዐዋቂና አስተዋይ መሪ ሲኖረው ግን ለረዥም ጊዜ ጽኑ ሕዝብ ይሆናል።


ለሌሎች ሰዎች ደንታ የሌላቸው ፌዘኞች በከተማ ውስጥ ብጥብጥ ያነሣሣሉ፤ ጠቢባን ግን የደፈረሰውን ጸጥታ መልሰው ያረጋጋሉ።


በዚያች ከተማ የሚኖር ጥበበኛ የሆነ አንድ ድኻ ሰው ከተማይቱን በጥበቡ አዳናት፤ ይሁን እንጂ ያንን ድኻ ማንም አላስታወሰውም።


ምላስም እንደ እሳት ናት፤ ምላስ በአካል ክፍሎቻችን መካከል የምትገኝ ክፉ ዓለም ናት፤ አካላችንን ትበክላለች፤ ከገሃነም እንደሚወጣ እሳትም የኑሮአችንን ሂደት ሁሉ ታቃጥላለች።


跟着我们:

广告


广告