Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




አብድዩ 1:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 “እኔ እግዚአብሔር በአሕዛብ ሁሉ ላይ የምፈርድበት ቀን ደርሶአል፤ ኤዶም ሆይ! እንደ ሥራህ ዋጋህን ታገኛለህ፤ የምትፈጽመው ክፉ ሥራ በራስህ ላይ ይመለሳል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 “በአሕዛብ ሁሉ ላይ፣ የእግዚአብሔር ቀን ደርሷል፤ አንተ እንዳደረግኸው፣ በአንተም ላይ ይደረጋል፤ ክፉ ሥራህም በራስህ ላይ ይመለሳል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 የጌታ ቀን በአሕዛብ ሁሉ ላይ ቀርቧልና፥ አንተ እንዳደረግኸው እንዲሁ ይደረግብሃል፥ ፍዳህም በራስህ ላይ ይመለሳል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀን በአ​ሕ​ዛብ ሁሉ ላይ ቀር​ቦ​አ​ልና፥ አንተ እንደ አደ​ረ​ግ​ኸው እን​ዲሁ ይደ​ረ​ግ​ብ​ሃል፤ ፍዳ​ህም በራ​ስህ ላይ ይመ​ለ​ሳል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 የእግዚአብሔር ቀን በአሕዛብ ሁሉ ላይ ቀርቦአልና፥ አንተ እንዳደረግኸው እንዲሁ ይደረግብሃል፥ ፍዳህም በራስህ ላይ ይመለሳል።

参见章节 复制




አብድዩ 1:15
28 交叉引用  

ነገር ግን አስቴር ወደ ንጉሡ ቀረበች፤ ንጉሡም ትእዛዙን በጽሑፍ እንዲተላለፍ አደረገ፤ ያም ትእዛዝ ባስገኘው ውጤት ሃማን አይሁድን ለመደምሰስ ዐቅዶት የነበረው ሤራ በራሱ ላይ እንዲመለስበት ሆነ፤ እርሱና ዐሥር ልጆቹ በእንጨት ላይ ተሰቀሉ።


“ሁሉን የሚችል አምላክ ፍርድ የሚሰጥበትን ጊዜ ለምን አይወስንም? የእርሱ ታማኞችስ የፍርዱን ቃል እስከ መቼ ይጠባበቃሉ?


ባቢሎን ሆይ! አፍራሽዋ ባቢሎን! በእኛ ላይ ያደረግሽብንን የክፋት ብድራት ሁሉ በአንቺ ላይ የሚመልስብሽ የተባረከ ነው።


ኃጢአተኛን ሰው የገዛ ራሱ ክፋት ያጠምደዋል፤ በኃጢአቱም ገመድ ይታሰራል።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ለሕዝቤ ለእስራኤል የሰጠኋቸውን ምድር ስላጠፉት ስለ እስራኤል ጐረቤቶችም የምናገረው ነገር አለኝ፤ እነዚያን ክፉ ሕዝቦች ከየአገራቸው ነቃቅዬ እወስዳቸዋለሁ፤ የይሁዳንም ሕዝብ ከመካከላቸው መንጥቄ አወጣቸዋለሁ።


“እንግዲህ መቀጣት የማይገባቸው ሰዎች እንኳ የቅጣቱን ጽዋ ገፈት የሚቀምሱ ከሆነ እናንተ ያለ ቅጣት የምታመልጡ ይመስላችኋልን? አይደለም፤ እናንተም ከቅጣቱ ጽዋ መጠጣት አለባችሁ።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ቀስት መደገን የሚችሉትን ቀስተኞች በባቢሎን ላይ ይዘምቱ ዘንድ ጥሩአቸው፤ ከተማይቱን ይክበቡ፤ ማንም እንዳያመልጥ ተጠባበቁ፤ የክፉ ሥራዋንም ዋጋ ክፈሉአት፤ በሌሎች ላይ የፈጸመችውንም ግፍ በእርስዋም ላይ ፈጽሙባት፤ እርስዋ በእስራኤል ቅዱስ በእኔ ላይ ተዳፍራለች፤


አጥፊዎች በባቢሎን ላይ ስለ ዘመቱ ወታደሮችዋ ተማረኩ፤ ቀስታቸውም ተሰባበረ፤ እኔ ለሁሉም እንደየሥራው ዋጋውን የምከፍል አምላክ ስለ ሆንኩ፥ ባቢሎን በፈጸመችው ግፍ መጠን ፍዳዋን እከፍላታለሁ።


የደመና ቀን ቀርቦአል፤ ይህም የእግዚአብሔር የፍርድ ቀን ነው! እርሱም ለሕዝቦች የመከራ ቀን ይሆናል።


ስለዚህም እኔ ልዑል እግዚአብሔር ሕያው እንደ መሆኔ በሕዝቤ ላይ ባላችሁ ጥላቻ ምክንያት ያሳያችሁት ቊጣና ምቀኝነት ሁሉ ተገቢውን ቅጣት እሰጣችኋለሁ። እነርሱም እናንተን በምቀጣበት ጊዜ የምቀጣችሁ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን እንዲያውቁ አደርጋለሁ።


የእስራኤል ምድር ባድማ በመሆኑ እንደ ተደሰታችሁ እኔም የሴኢርን ተራራና የኤዶምን ግዛት ሁሉ ባድማ አደርጋለሁ፤ ከዚያ በኋላ ሁሉም እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃል።”


ወዮ! የጌታ ቀን ቀርቦአል! ሁሉን ቻይ እግዚአብሔር ጥፋትን የሚያመጣበት ቀን ደርሶአል። ስለዚያ ቀን ወዮ!


በጽዮን መለከት ንፉ! በተቀደሰው ተራራውም ላይ የእሪታ ድምፅ አሰሙ! የጌታ ቀን መምጫ ስለ ተቃረበ በምድሪቱ የሚኖሩ ሁሉ ይንቀጥቀጡ።


እግዚአብሔር እንደ ነጐድጓድ ያለ ድምፁን በሠራዊቱ ላይ ያሰማል፤ ሠራዊቱ ምንኛ ብዙ ነው! ትእዛዙን የሚቀበሉ ከቊጥር በላይ ናቸው፤ በእርግጥም የእግዚአብሔር ቀን ታላቅ ነው፤ በጣም አስፈሪ ስለ ሆነ በዚያ ቀን ማን ችሎ ይቆማል?


እናንተ የእግዚአብሔርን ቀን መምጣት የምትጠባበቁ ወዮላችሁ! ያ ቀን የጨለማ እንጂ የብርሃን ቀን ስላይደለ ለምን ያንን ቀን ትጠባበቃላችሁ?


በእግዚአብሔር የፍርድ ቀን ጨለማ እንጂ ብርሃን አይሆንላችሁም፤ ያ ቀን ምንም ብርሃን የማይታይበት ድቅድቅ ጨለማ ይሆንባችኋል።


ለእኔ አልታዘዝም ያሉትን መንግሥታት ሁሉ በታላቅ ቊጣዬ እበቀላቸዋለሁ።”


የብዙ ሕዝቦችን ንብረት ስለ ዘረፋችሁ ከእነርሱ የተረፉት የእናንተን ንብረት ይዘርፋሉ፤ ይህም የሚሆነው እናንተ ሰዎችን ስለ ገደላችሁ፥ ምድሪቱን ከተሞችንና በእነርሱ የሚኖሩትን ስላጠፋችሁ ነው።


በሌሎች ላይ በምትፈርዱበት ፍርድ፥ በእናንተም ላይ ይፈረድባችኋል፤ እንዲሁም በምትሰፍሩበት መስፈሪያ ይሰፈርባችኋል።


የእግዚአብሔር ፍርድ ምሕረት ለማያደርግ ሰው ምሕረት አያደርግም፤ ሆኖም ምሕረት ፍርድን ያሸንፋል።


አዶኒቤዜቅም “የእጆቻቸውና የእግሮቻቸው አውራ ጣቶች የተቈረጡባቸው ሰባ ነገሥታት ከገበታዬ ሥር ፍርፋሪ እየለቀሙ ይበሉ ነበር፤ በእነርሱ ላይ የፈጸምኩትን ግፍ ዛሬ እግዚአብሔር በእኔ ላይ መልሶ አመጣብኝ” ሲል ተናገረ። ወደ ኢየሩሳሌምም ተወስዶ በዚያው ሞተ።


跟着我们:

广告


广告