ዘኍል 9:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም21 አንዳንድ ጊዜ ደመናው የሚቈየው ከምሽት እስከ ንጋት ብቻ ነበር፤ ስለዚህ ደመናው እንደ ተነሣ ወዲያውኑ ጒዞ ይቀጥላሉ፤ ወይም ደመናው ቀንና ማታ ቢቈይ ደመናው ሲነሣ ይሄዱ ነበር። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም21 አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ደመናው ከምሽት እስከ ንጋት ብቻ ይቈያል፤ ደመናው ንጋት ላይ ሲነሣም ጕዟቸውን ይጀምራሉ፤ ቀንም ይሁን ሌሊት ደመናው ከተነሣ ጕዞ ይጀምራሉ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)21 አንዳንድ ጊዜም ደመናው ከማታ ጀምሮ እስከ ጥዋት ድረስ ይቈይ ነበር፤ በጥዋትም ደመናው በተነሣ ጊዜ ይጓዛሉ፥ ወይም ባለማቋረጥ ቀኑንም ሌሊቱንም የሚቈይ ቢሆን፥ ደመናው በተነሣ ጊዜ ይጓዙ ነበር። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)21 አንዳንድ ጊዜም ደመናው ከማታ ጀምሮ እስከ ጥዋት ድረስ ይቀመጥ ነበር፤ በጥዋትም ደመናው በተነሣ ጊዜ ይጓዙ ነበር። በቀንም በሌሊትም ቢሆን ደመናው በተነሣ ጊዜ ይጓዙ ነበር 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)21 አንዳንድ ጊዜም ደመናው ከማታ ጀምሮ እስከ ጥዋት ድረስ ይቀመጥ ነበር፤ በጥዋትም ደመናው በተነሣ ጊዜ ይጓዙ ነበር፤ በቀንም በሌሊትም ቢሆን፥ ደመናው በተነሣ ጊዜ ይጓዙ ነበር። 参见章节 |