Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 8:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ስለዚህ እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት፥ ሙሴና አሮን እንዲሁም የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ሌዋውያንን ቀደሱ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ሙሴና አሮን እንዲሁም የእስራኤል ማኅበረ ሰብ ሁሉ እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት በሌዋውያኑ አደረጉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ሙሴና አሮን የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ እንዲሁ በሌዋውያን ላይ አደረጉ፤ ጌታ ሙሴን ስለ ሌዋውያን እንዳዘዘው እንዲሁ የእስራኤል ልጆች አደረጉላቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ሙሴና አሮን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ማኅ​በር ሁሉ እን​ዲሁ በሌ​ዋ​ው​ያን ላይ አደ​ረጉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን ስለ ሌዋ​ው​ያን እን​ዳ​ዘ​ዘው እን​ዲሁ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አደ​ረ​ጉ​ላ​ቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ሙሴና አሮን የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ እንዲሁ በሌዋውያን ላይ አደረጉ፤ እግዚአብሔር ሙሴን ስለ ሌዋውያን እንዳዘዘው እንዲሁ የእስራኤል ልጆች አደረጉላቸው።

参见章节 复制




ዘኍል 8:20
7 交叉引用  

እስራኤላውያን ሁሉ ታዛዦች በመሆን እግዚአብሔር በሙሴና በአሮን አማካይነት ያዘዘውን ሁሉ ለመፈጸም ዝግጁዎች ሆኑ፤


በዚህ ፈንታ ሌዋውያንን በመገናኛው ድንኳንና በውስጡም ባሉት የመገልገያ ዕቃዎች ላይ ኀላፊዎች አድርገህ መድባቸው፤ እነርሱ ድንኳኑንና በውስጡ ያሉትን የመገልገያ ዕቃዎች ሁሉ ይሸከማሉ፤ በድንኳኑም ውስጥ ያገለግላሉ፤ በዙሪያውም ይሰፍራሉ።


ስለዚህ የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ሁሉን ነገር አደረጉ።


የእስራኤልን ሕዝብ ወክለው በመገናኛው ድንኳን ውስጥ እንዲያገለግሉና እስራኤላውያን ወደ ተቀደሰው ስፍራ በመቅረብ እንዳይቀሠፉ ይጠብቁአቸው ዘንድ፥ ሌዋውያንን ከእስራኤላውያን እንደ ስጦታ ተቀብዬ ለአሮንና ለልጆቹ ሰጥቻለሁ።”


ሌዋውያንም ራሳቸውን አነጹ፤ ልብሳቸውንም አጠቡ፤ አሮንም ለእግዚአብሔር ልዩ ስጦታ አድርጎ ለእግዚአብሔር ለያቸው የመንጻቱንም ሥርዓት ፈጸመላቸው፤


ሁለት ቀንም ይሁን አንድ ወር፥ አንድ ዓመትም ይሁን ከዚያ የረዘመ ጊዜ ደመናው በድንኳኑ ላይ እስካረፈበት ጊዜ ድረስ አይንቀሳቀሱም ነበር፤ ደመናው ሲነሣ ግን ጒዞአቸውን ይቀጥሉ ነበር።


እነርሱም የመጀመሪያው ወር በገባ በዐሥራ አራተኛው ቀን በምሽት በሲና ምድረ በዳ በዓሉን አከበሩ፤ እስራኤላውያን እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ሁሉን ነገር አደረጉ።


跟着我们:

广告


广告