Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 7:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ከዚያ በኋላ በእስራኤል ነገዶች መካከል የጐሣ አለቆች የሆኑት ማለትም በሕዝብ ቈጠራ ጊዜ ኀላፊነት የነበራቸው ሁሉ፥

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ከዚያም የእስራኤል አለቆች ሆነው ከተቈጠሩት ነገዶች ኀላፊዎች የነበሩት የየቤተ ሰቡ መሪዎች ስጦታቸውን አቀረቡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ከተቈጠሩት በላይ የተሾሙት የነገዶች አለቆች የነበሩት የእስራኤል አለቆች፥ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች ቁርባናቸውን አቀረቡ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ዐሥራ ሁለቱ የእ​ስ​ራ​ኤል አለ​ቆች፥ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች አለ​ቆች፥ ቍር​ባ​ና​ቸ​ውን አቀ​ረቡ፤ እነ​ዚ​ህም ከተ​ቈ​ጠ​ሩት በላይ የተ​ሾሙ የነ​ገ​ዶች አለ​ቆች ነበሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 የእስራኤል አለቆች፥ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች፥ ቍርባናቸውን አቀረቡ፤ እነዚህም ከተቈጠሩት በላይ የተሾሙ የነገዶች አለቆች ነበሩ።

参见章节 复制




ዘኍል 7:2
11 交叉引用  

ከዚህ በኋላ ሰሎሞን የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት የዳዊት ከተማ ከሆነችው ከጽዮን ለማምጣትና ወደ ቤተ መቅደሱ ለማስገባት የእስራኤል የነገድ መሪዎችና የጐሣ አለቆች ሁሉ እርሱ ወደሚገኝበት ወደ ኢየሩሳሌም እንዲሰበሰቡ ጠራ፤


የንጉሡ ባለሟሎች የሆኑ ባለሥልጣኖችም መሥዋዕት ሆነው የሚቀርቡ እንስሶችን በገዛ ፈቃዳቸው ለምእመናን፥ ለካህናትና ለሌዋውያን ሰጡ፤ የቤተ መቅደሱ አለቆች የሆኑት ሊቃነ ካህናቱ ሒልቂያ፥ ዘካርያስና ይሒኤልም የፋሲካ መሥዋዕት ሆነው የሚቀርቡ ሁለት ሺህ ስድስት መቶ የበግና የፍየል ጠቦቶችንና ሦስት መቶ በሬዎችን ለካህናት ሰጡ፤


አለቆችም በተቀደሰው ኤፉድና በደረት ኪስ ላይ የሚሆኑ መረግድና ሌሎችም ጌጣጌጦች፥


ሙሴ ለእስራኤል የነገድ መሪዎች አላቸው፤ እግዚአብሔር ያዘዘው ነገር ይህ ነው፦


ሙሴና አልዓዛር በጌጣጌጥ መልክ ተሠርቶ የነበረውን ወርቅ ሁሉ ተቀበሉ።


跟着我们:

广告


广告