Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 5:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ካህኑ የዱቄቱን መባ ከሴትዮዋ እጅ ወስዶ ለእግዚአብሔር በመወዝወዝ የሚቀርብ የተለየ መሥዋዕት ይሆን ዘንድ በመሠዊያው ላይ ያቅርበው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ካህኑ ለቅናት የቀረበውን የእህል ቍርባን ይቀበላት፤ በእግዚአብሔር ፊት ወዝውዞ ወደ መሠዊያው ያቅርበው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ካህኑም የቅንዓቱን የእህል ቁርባን ከሴቲቱ እጅ ይወስዳል፥ የእህሉንም ቁርባን በጌታ ፊት ይወዘውዘዋል፥ ወደ መሠዊያውም ያመጣዋል፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ካህ​ኑም የቅ​ን​ዐ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት ከሴ​ቲቱ እጅ ይወ​ስ​ዳል፤ ያንም መሥ​ዋ​ዕት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያቀ​ር​በ​ዋል፥ ወደ መሠ​ዊ​ያ​ውም ያመ​ጣ​ዋል፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ካህኑም የቅንዓቱን የእህል ቍርባን ከሴቲቱ እጅ ይወስዳል፥ የእህሉንም ቍርባን በእግዚአብሔር ፊት ይወዘውዘዋል፥ ወደ መሠዊያውም ያመጣዋል፤

参见章节 复制




ዘኍል 5:25
6 交叉引用  

ይህን ሁሉ ምግብ በአሮንና በልጆቹ እጅ ላይ አኑር፤ እርሱንም ወዝውዘው ለእኔ ለእግዚአብሔር የሚቀርብ መሥዋዕት አድርገው ያቅርቡት።


ይህን ሁሉ ምግብ ወስዶ ለአሮንና ለልጆቹ በእጃቸው አስያዛቸው፤ አነርሱም በመወዝወዝ ለእግዚአብሔር ልዩ መባ አድርገው አቀረቡት።


ያ ሰው ሚስቱን ወደ ካህኑ ያምጣት፥ ስለ እርስዋ የሚፈልገውንም አንድ ኪሎ የገብስ ዱቄት ቊርባን ያምጣ፤ የቅናት ቊርባን ማለት በደልን የሚገልጥ የእህል ቊርባን ስለ ሆነ ዘይት አያፍስስበት፤ ዕጣንም አያድርግበት።


ካህኑም ሴትዮዋን በእግዚአብሔር ፊት ያቁማት፤ የራስዋንም ጠጒር ይፍታ፤ የቅናቱንም የእህል ቊርባን በእጅዋ ላይ ያስቀምጥ፤ በእጁም እርግማንን የሚያመጣ መራራ ውሃ ይያዝ።


ሴትዮዋ ብርቱ ሕመም የሚያስከትልባትን መራራ ውሃ እንድትጠጣ ከማድረጉ በፊት፥


ከዚህም በኋላ ከእህሉ ቊርባን አንድ እፍኝ ወስዶ የመታሰቢያ ቊርባን ይሆን ዘንድ በመሠዊያው ላይ ያቃጥለው፤ በመጨረሻም ሴትዮዋ ውሃውን እንድትጠጣው ያድርግ።


跟着我们:

广告


广告