Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 5:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ከዚያም ካህኑ እንዲህ ብሎ ያስምላት፦ ከባልሽ ጋር እያለሽ ሌላ ወንድ ከአንቺ ጋር የተኛ ባይሆን፥ ራስሽንም ባታረክሺ ርግማን ከሚያመጣው ከዚህ መራራ ውሃ ነጻ ሁኚ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ካህኑም ሴትዮዋን ያስምላታል፤ እንዲህም ይላታል፤ “ሌላ ወንድ ዐብሮሽ ካልተኛ፣ በትዳር ላይ ሆነሽ ወደ ርኩሰት ካላዘነበልሽ ይህ ርግማን የሚያመጣ መራራ ውሃ ጕዳት አያድርስብሽ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ሴቲቱንም እንዲህ ብሎ ካህኑ ያምላታል፦ ‘ከአንቺ ጋር ሌላ ወንድ ካልተኛ፥ በባልሽም ሥልጣን ሥር እየነበርሽ ራስሽን ለማርከስ ዘወር ካላልሽ፥ እርግማንን ከሚያመጣው ከዚህ መራራ ውኃ የተጠበቅሽ ሁኚ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ካህ​ኑም ያም​ላ​ታል፤ ሴቲ​ቱ​ንም እን​ዲህ ይላ​ታል፦ ሌላ ወንድ አል​ተ​ኛሽ፥ ባል​ሽ​ንም አል​ተ​ውሽ፥ ራስ​ሽ​ንም አላ​ረ​ከ​ስሽ እንደ ሆነ፥ ርግ​ማ​ንን ከሚ​ያ​መጣ ከዚህ መራራ ውኃ ንጹሕ ሁኚ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ካህኑም ያምላታል፥ ሴቲቱንም እንዲህ ይላታል፦ ሌላ ወንድ አልተኛሽ፥ ባልሽንም አልተውሽ፥ ራስሽንም አላረከስሽ እንደ ሆነ፥ እርግማንን ከሚያመጣ ከዚህ መራራ ውኃ ንጹሕ ሁኚ፤

参见章节 复制




ዘኍል 5:19
5 交叉引用  

“ለእስራኤላውያን እንዲህ በላቸው፦ የአንድ ሰው ሚስት ጠባይዋ ተበላሽቶ በእርሱ ላይ እምነተቢስ ልትሆን ትችላለች፤


ካህኑም ሴትዮዋን በእግዚአብሔር ፊት ያቁማት፤ የራስዋንም ጠጒር ይፍታ፤ የቅናቱንም የእህል ቊርባን በእጅዋ ላይ ያስቀምጥ፤ በእጁም እርግማንን የሚያመጣ መራራ ውሃ ይያዝ።


ምንም በደል ያልሠራች ንጽሕት ሆና ከተገኘች ግን ምንም ጒዳት አይደርስባትም፤ ልጆችንም መውለድ ትችላለች።


ኢየሱስ ግን ዝም አለ። የካህናት አለቃውም እንደገና ኢየሱስን “በሕያው እግዚአብሔር ስም ይዤሃለሁ! አንተ የእግዚአብሔር ልጅ መሲሕ እንደ ሆንክ ንገረን!” አለው።


ለምሳሌ፥ ያገባች ሴት ባልዋ በሕይወት እስካለ ድረስ ከእርሱ ጋር በሕግ የታሰረች ናት፤ ባልዋ ከሞተ ግን ከታሰረችበት ሕግ ነጻ ናት።


跟着我们:

广告


广告