ዘኍል 35:30 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም30 “በግድያ ወንጀል የተከሰሰ ማንኛውም ሰው የሞት ፍርድ ሊበየንበት የሚችለው ሁለት ወይም ከሁለት በላይ የሆኑ ሰዎች የመሰከሩበት እንደ ሆነ ነው፤ የአንድ ሰው ምስክርነት ግን ለግድያ ወንጀል የተከሰሰውን ሰው ሊያስጠይቀው አይችልም። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም30 “ ‘ሰው የገደለ ማንኛውም ሰው በሞት የሚቀጣው ምስክሮች ሲመሰክሩበት ብቻ ነው፤ ይሁን እንጂ ማንም ሰው በአንድ ምስክር ብቻ በሞት አይቀጣም። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)30 ነፍሰ ገዳይ ሁሉ ምስክሮች በሰሚጡት ቃል ይገደላል፤ በአንድ ምስክር ግን ማናቸውንም ሰው መግደል አይገባም። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)30 ነፍሰ ገዳይ ሁሉ በምስክሮች ቃል ይገደላል፤ በአንድ ምስክር ግን ማናቸውንም ሰው መግደል አይገባም። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)30 ነፍሰ ገዳይ ሁሉ በምስክሮች አፍ ይገደላል፤ በአንድ ምስክር ግን ማናቸውንም ሰው መግደል አይገባም። 参见章节 |