Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 31:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 የእስራኤል ሕዝብ ምድያማውያን ሴቶችንና ሕፃናትን ማረኩ፤ የከብት፥ የበግና የፍየል መንጋዎቻቸውን ወሰዱ፤ ሀብታቸውን ሁሉ በዘበዙ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ከዚያም እስራኤላውያን የምድያማውያንን ሴቶችና ሕፃናት ማረኩ፤ የቀንድ ከብቶቻቸውን፣ የበግና የፍየል መንጋዎቻቸውን ሁሉ ነዱ፤ ሀብታቸውንም በሙሉ ወሰዱ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 የእስራኤልም ልጆች የምድያምን ሴቶችና ልጆቻቸውን ማረኩ፤ እንስሶቻቸውንና መንጎቻቸውንም ዕቃቸውንም ሁሉ በዘበዙ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 የም​ድ​ያ​ም​ንም ሴቶ​ችና ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ማረኩ፤ እን​ስ​ሶ​ቻ​ቸ​ው​ንና ዕቃ​ቸ​ውን፥ ንብ​ረ​ታ​ቸ​ው​ንና ኀይ​ላ​ቸ​ውን በዘ​በዙ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 የእስራኤልም ልጆች የምድያምን ሴቶችና ልጆቻቸውን ማረኩ፤ እንስሶቻቸውንና መንጎቻቸውንም ዕቃቸውንም ሁሉ በዘበዙ።

参见章节 复制




ዘኍል 31:9
9 交叉引用  

ሴቶችንና ሕፃናትን ማረኩ፤ በየቤቱ ያገኙትን ሀብት ሁሉ ዘረፉ።


እንዲሁም በአንዳንድ እረኞች ሰፈር ላይ አደጋ በመጣል ብዙ በጎችን፥ ፍየሎችንና ግመሎችን ማረኩ፤ ከዚህም በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሰው ሄዱ።


ንጉሥ አካዝ ኃጢአት ስለ ሠራ የሶርያ ንጉሥ ድል እንዲያደርገውና ብዙ ወገኖቹን እስረኞች አድርጎ ወደ ደማስቆ እንዲወስድ እግዚአብሔር ፈቀደ፤ እንዲሁም የረማልያ ልጅ የሆነው የእስራኤል ንጉሥ ፋቁሔ አካዝን ድል እንዲያደርግና እጅግ በጣም ጀግኖች ከሆኑ ከይሁዳ ወታደሮች መካከል በአንድ ቀን መቶ ኻያ ሺህ እንዲገድል እግዚአብሔር ፈቀደ፤ የቀድሞ አባቶቻቸው አምላክ እግዚአብሔር ይህን የፈቀደበት ምክንያት የይሁዳ ሰዎች እርሱን ስለ ተዉ ነው።


ከተሞቻቸውንና የሰፈሩበትን ቦታ ሁሉ አቃጠሉ፤


የጦር ሹማምንት ያልሆኑት ወታደሮች ግን ያመጡትን ምርኮ ለራሳቸው አስቀሩ።


አምስቱንም የምድያም ነገሥታት ኤዊን፥ ሬቄምን፥ ጹርን፥ ሑርንና ሬባዕን ገደሉ፤ የቢዖርን ልጅ በለዓምንም ገደሉት።


ሆኖም ሴቶችንና ሕፃናት ልጆችን፥ እንስሶችንና በከተማይቱ ውስጥ ያለውን ንብረት ሁሉ ለራስህ ማርከህ ትወስዳለህ፤ የጠላቶችህ ንብረት የሆነውን ሁሉ ልትጠቀምበት ትችላለህ፤ እግዚአብሔር አምላክህ እርሱን ለአንተ አሳልፎ ሰጥቶሃል።


跟着我们:

广告


广告