Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 27:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 መላው የእስራኤል ማኅበር እርሱን ይታዘዙት ዘንድ የሥልጣንህ ተካፋይ አድርገው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 መላው የእስራኤል ማኅበረ ሰብ እንዲታዘዝለትም ከሥልጣንህ ከፍለህ ስጠው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ እንዲታዘዙት ከክብርህ አኑርበት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ እን​ዲ​ታ​ዘ​ዙት ከክ​ብ​ርህ ስጠው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ እንዲታዘዙት ከክብርህ አኑርበት።

参见章节 复制




ዘኍል 27:20
11 交叉引用  

ከኢያሪኮ የመጡት ነቢያት እርሱን ባዩት ጊዜ “በኤልያስ ላይ ዐድሮ የነበረው የመንፈስ ኀይል በኤልሳዕ ላይ አርፏል!” አሉ፤ ወደ እርሱም በመቅረብ ጐንበስ ብለው እጅ ነሡት


በዚህ ዐይነት ሰሎሞን በአባቱ እግር ተተክቶ እግዚአብሔር ባጸናው ዙፋን ላይ ተቀመጠ፤ እርሱም ሁሉ ነገር የተሳካለት ንጉሥ ሆነ፤ መላውም የእስራኤል ሕዝብ ታዘዙለት፤


እግዚአብሔር በአገሪቱ ሕዝብ ሁሉ ፊት ሰሎሞንን ከፍ ከፍ አደረገው፤ ከዚህ በፊት እስራኤልን ከገዛ ከማንኛውም ንጉሥ ይበልጥ የተከበረ እንዲሆንም አደረገው።


እኔም ወደዚያ ወርጄ ከአንተ ጋር እነጋገራለሁ፤ ለአንተም ከሰጠሁህ መንፈስ ከፍዬ ለእነርሱ እሰጣቸዋለሁ፤ ከዚያም በኋላ በእነዚህ ሕዝብ ላይ ያለህን ኀላፊነት በመሸከም ይረዱሃል፤ ከእንግዲህም ወዲህ ይህን ሁሉ ኀላፊነት ብቻህን አትሸከምም።


በካህኑ በአልዓዛርና በመላው ማኅበር ፊት እንዲቆም አድርገው፤ በእነርሱም ሁሉ ፊት የአንተ ተተኪ መሆኑን አስታውቅ።


ካህኑ አልዓዛር በኡሪም አማካይነት ፈቃዴን የሚያውቅ ስለ ሆነ ኢያሱ በአልዓዛር ይደገፋል፤ በዚህም ዐይነት አልዓዛር ኢያሱንና መላውን የእስራኤል ማኅበር በተግባር አፈጻጸማቸው ሁሉ ይመራቸዋል።”


በድንገት የእግዚአብሔር መንፈስ በአንተ ላይ በኀይል ይወርዳል፤ ከእነርሱም ጋር ትንቢት መናገር ትጀምራለህ፤ ልዩ ሰውም ትሆናለህ፤


ሳኦልም ከሳሙኤል ተለይቶ በሄደ ጊዜ እግዚአብሔር ሳኦልን ሌላ አዲስ ሰው አደረገው፤ ሳሙኤል በምልክት የነገረውም ሁሉ በዚያን ቀን ተፈጸመ።


跟着我们:

广告


广告