Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 26:59 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

59 ዓሞራም በግብጽ የተወለደችውን የሌዊን ሴት ልጅ ዮኬቤድን አግብቶ ነበር፤ እርስዋም አሮንና ሙሴ የተባሉትን ሁለት ወንዶች ልጆችንና ማርያም የተባለችውን አንዲት ሴት ልጅ ወለደችለት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

59 የእንበረም ሚስቱ ዮካብድ ትባል ነበር፤ እርሷም በግብጽ አገር ከሌዋውያን የተወለደች የሌዊ ዘር ነበረች። ከእንበረምም አሮንን፣ ሙሴንና እኅታቸውን ማርያምን ወለደች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

59 የእንበረም ሚስት ስም ዮካብድ ነበረ። እርሷ በግብጽ ከሌዊ የተወለደች የሌዊ ልጅ ነበረች፤ ለእንበረምም አሮንንና ሙሴን እኅታቸውንም ማርያምን ወለደችለት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

59 የቆሬ ወገን፥ የቀ​ዓት ወገን። ቀዓ​ትም እን​በ​ረ​ምን ወለደ። በግ​ብፅ ሀገር እነ​ዚ​ህን ሌዋ​ው​ያ​ንን የወ​ለ​ደ​ቻ​ቸው የሌዊ ልጅ የእ​ን​በ​ረም ሚስት ስም ዮካ​ብድ ነበረ። ለእ​ን​በ​ረ​ምም አሮ​ን​ንና ሙሴን እኅ​ታ​ቸ​ው​ንም ማር​ያ​ምን ወለ​ደ​ች​ለት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

59 የእንበረም ሚስት ስም ዮካብድ ነበረ። እርስዋ በግብፅ ከሌዊ የተወለደች የሌዊ ልጅ ነበረች፤ ለእንበረምም አሮንንና ሙሴን እኅታቸውንም ማርያምን ወለደችለት።

参见章节 复制




ዘኍል 26:59
7 交叉引用  

የአሮን እኅት ነቢይቱ ማርያም ከበሮዋን አነሣች፤ ሌሎችም ሴቶች ከበሮዎቻቸውን እየመቱና እየጨፈሩ ይከተሉአት ጀመር፤


የሕፃኑም እኅት የሚደርስበትን ነገር ለማየት ራቅ ብላ ትጠባበቀው ነበር።


ዓምራም ዮኬቤድ የተባለችውን የአባቱን እኅት አገባ፤ እርስዋም አሮንንና ሙሴን ወለደችለት። ዓምራም በሕይወት የኖረበት ዘመን 137 ዓመት ነው።


አክስትህ ስለ ሆነች ከአባትህ እኅት ጋር ፍትወታዊ ግንኙነት አታድርግ።


ሙሴ ከኩሽ ነገድ የሆነች (ኢትዮጵያዊት) ሴት በማግባቱ ምክንያት ማርያምና አሮን በሐሜት እንዲህ ሲሉ ነቀፉት፦


በመጀመሪያው ወር መላው የእስራኤል ማኅበር ወደ ጺን ምድረ በዳ መጥተው በቃዴስ ሰፈሩ፤ ማርያምም ስለሞተች በዚያው ተቀበረች።


跟着我们:

广告


广告