ዘኍል 25:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 ከምድያማዊቱ ሴት ጋር የተገደለው እስራኤላዊ ስም የሳሉ ልጅ ዚምሪ ሲሆን እርሱም በስምዖን ነገድ ውስጥ የጐሣ አለቃ ነበር። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም14 ከምድያማዊቷ ሴት ጋራ የተገደለው እስራኤላዊ የሰሉ ልጅ ዘንበሪ ይባላል፤ የስምዖናውያን ቤተ ሰብ አለቃ ነበር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 ከምድያማዊቱም ጋር የተገደለው የእስራኤላዊው ሰው ስም ዘንበሪ ይባል ነበረ፤ እርሱም የስምዖናውያን ወገን የአባቱ ቤት አለቃ የሆነ የሰሉ ልጅ ነበረ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 ከምድያማዊቱም ጋር የተገደለው የእስራኤላዊው ሰው ስም ዘንበሪ ነበረ፤ የአባቱ ቤት አለቃ የስምዖናውያን የሆነ የሰሉ ልጅ ነበረ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 ከምድያማዊቱም ጋር የተገደለው የእስራኤላዊው ሰው ስም ዘንበሪ ነበረ፤ የአባቱ ቤት አለቃ የስምዖናውያን የሆነ የሰሉ ልጅ ነበረ። 参见章节 |
የእስራኤል ነገዶች አስተዳዳሪዎች ስም ዝርዝር እንደሚከተለው ነው፦ የሮቤል ነገድ አስተዳዳሪ፦ የዚክሪ ልጅ ኤሊዔዘር የስምዖን ነገድ አስተዳዳሪ፦ የማዕካ ልጅ ሸፋጥያ የሌዊ ነገድ አስተዳዳሪ፦ የቀሙኤል ልጅ ሐሻብያ የአሮን ነገድ አስተዳዳሪ፦ ሳዶቅ የይሁዳ ነገድ አስተዳዳሪ፦ ከንጉሥ ዳዊት ወንድሞች አንዱ የሆነው ኤሊሁ የይሳኮር ነገድ አስተዳዳሪ፦ የሚካኤል ልጅ ዖምሪ የዛብሎን ነገድ አስተዳዳሪ፦ የአብድዩ ልጅ ዩሽማዕያ የንፍታሌም ነገድ አስተዳዳሪ፦ የዐዝርኤል ልጅ ያሪሞት የኤፍሬም ነገድ አስተዳዳሪ፦ የዐዛዝያ ልጅ ሆሴዕ የምዕራባዊ የምናሴ ነገድ እኩሌታ አስተዳዳሪ፦ የፐዳያ ልጅ ኢዮኤል የምሥራቃዊ የምናሴ ነገድ እኩሌታ አስተዳዳሪ፦ የዘካርያስ ልጅ ዩዶ የብንያም ነገድ አስተዳዳሪ፦ የአበኔር ልጅ ያዕሲኤል የዳን ነገድ አስተዳዳሪ፦ የይሮሐም ልጅ ዐዛርኤል።