Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 24:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ‘ባላቅ በቤተ መንግሥቱ ያለውን ብርና ወርቅ ሁሉ ቢሰጠኝ እንኳ በራሴ ፈቃድ ደግ ወይም ክፉ ነገር አደርግ ዘንድ የእግዚአብሔርን ቃል መተላለፍ አልችልም፤ የምናገረው እግዚአብሔር እንድናገር የነገረኝን ነገር ብቻ ነው’ ብዬ ነግሬአቸው አልነበረምን?”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ‘ሌላው ይቅርና ባላቅ በብርና በወርቅ የተሞላ ቤተ መንግሥቱን ቢሰጠኝ እንኳ፣ እግዚአብሔር የሚለውን ብቻ ከመናገር በቀር ከእግዚአብሔር ትእዛዝ ውጭ በራሴ ሐሳብ በጎም ሆነ ክፉ ማድረግ አልችልም።’

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ‘ባላቅ በቤቱ የሞላውን ብርና ወርቅ ቢሰጠኝ፥ በራሴ ፈቃድ መልካምን ወይም ክፉን ነገር ለማድረግ የጌታን ቃል መተላለፍ አልችልም፤ ጌታ የተናገረውን እርሱን እናገራለሁ።’

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ባላቅ በቤቱ የሞ​ላ​ውን ብርና ወርቅ ቢሰ​ጠኝ፥ መል​ካ​ሙን ወይም ክፉ​ውን ከልቤ ለማ​ድ​ረግ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል እተ​ላ​ለፍ ዘንድ አይ​ቻ​ለ​ኝም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ና​ገ​ረ​ውን እር​ሱን እና​ገ​ራ​ለሁ ብዬ ወደ እኔ ለላ​ክ​ሃ​ቸው መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችህ አል​ተ​ና​ገ​ር​ኋ​ቸ​ው​ምን?

参见章节 复制




ዘኍል 24:13
6 交叉引用  

የእግዚአብሔር ነቢይ ግን “የሀብትህን እኩሌታ ብትሰጠኝ እንኳ ወደ ቤትህ አልሄድም፤ ከአንተ ጋር እህል ውሃም አልቀምስም።


ሚክያስ ግን “እግዚአብሔር የሚገልጥልኝን ቃል ብቻ እንደምናገር በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ!” ሲል መለሰለት።


በዚያን ጊዜ ሙሴ ለሕዝቡ እንዲህ አለ፦ “ይህን ሁሉ ሥራ እንዳከናውን እግዚአብሔር እኔን የላከኝ መሆኑን የምታውቁትና እኔ ይህን ሁሉ ሥራ የማከናውነው በራሴ ፈቃድ እንዳልሆነ የምትገነዘቡት በዚህ ነው፤


በለዓም ግን ለመልእክተኞቹ እንዲህ ሲል መልስ ሰጠ፤ “ባላቅ በቤተ መንግሥቱ የሚገኘውን ብርና ወርቅ ሁሉ ቢሰጠኝም በትንሽ ወይም በትልቅ ነገር የአምላኬን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ መተላለፍ አይቻለኝም፤


በዚያን ሌሊት እግዚአብሔር ወደ በለዓም መጣና “እነዚህ ሰዎች ወደ አንተ የመጡት ይዘውህ ሊሄዱ ከሆነ ተነሥተህ አብረሃቸው ሂድ፤ ነገር ግን እኔ የምነግርህን ብቻ አድርግ” አለው።


በለዓምም “እዚሁ ዕደሩና ነገ ጧት እግዚአብሔር የሚነግረኝን ሁሉ እነግራችኋለሁ” አላቸው፤ በዚህ ዐይነት የሞአባውያን መሪዎች ከበለዓም ጋር ቈዩ።


跟着我们:

广告


广告