ዘኍል 22:35 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም35 መልአኩ ግን “ከእነዚህ ሰዎች ጋር መሄዱን ሂድ፤ ነገር ግን እኔ የምነግርህን ብቻ ተናገር” አለው፤ በዚህ ዐይነት በለዓም ከባላቅ ባለሥልጣኖች ጋር ሄደ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም35 የእግዚአብሔርም መልአክ በለዓምን፣ “መሄዱን ከሰዎቹ ጋራ ሂድ፤ ነገር ግን እኔ የምነግርህን ብቻ ተናገር” አለው። ስለዚህ በለዓም ከባላቅ አለቆች ጋራ ሄደ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)35 የጌታም መልአክ በለዓምን፦ “ከሰዎቹ ጋር ሂድ፥ ነገር ግን የምነግርህን ቃል ብቻ ትናገራለህ” አለው። በለዓምም ከባላቅ ሹማምንት ጋር ሄደ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)35 የእግዚእብሔርም መልአክ በለዓምን፥ “ከሰዎቹ ጋር ሂድ፤ ነገር ግን የምናገርህን ቃል ብቻ ለመናገር ተጠንቀቅ” አለው። በለዓምም ከባላቅ አለቆች ጋር ሄደ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)35 የእግዚአብሔርም መልአክ በለዓምን፦ ከሰዎቹ ጋር ሂድ፥ ነገር ግን የምናገርህን ቃል ብቻ ትናገራለህ አለው። በለዓምም ከባላቅ አለቆች ጋር ሄደ። 参见章节 |