Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 19:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ሰው የገደለውን ወይም በሕመም የሞተውን ሰው በውጭ ወድቆ ሳለ ሬሳውን የሚነካ ሰው፥ ወይም የሰው ዐፅም፥ ወይም መቃብር የሚነካ ሰው ለሰባት ቀን የረከሰ ይሆናል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 “ሜዳ ላይ በሰይፍ የተገደለውን ወይም እንዲሁ የሞተውን ወይም ደግሞ ዐፅም ወይም መቃብር የሚነካ ማንኛውም ሰው እስከ ሰባት ቀን ድረስ የረከሰ ይሆናል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 በተንጣለለው ሜዳ በሰይፍ የተገደለውን ወይም የሞተውን በድን ወይም የሰውን ዐፅም ወይም መቃብር የሚነካ ማናቸውም ሰው ሰባት ቀን ርኩስ ይሆናል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 በሜ​ዳም የተ​ገ​ደ​ለ​ውን ወይም የሞ​ተ​ውን በድን፥ ወይም የሰ​ውን አጥ​ንት፥ ወይም መቃ​ብር የሚ​ነካ ሰባት ቀን ርኩስ ይሆ​ናል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 በሜዳም በሰይፍ የተገደለውን ወይም የሞተውን በድን ወይም የሰውን አጥንት ወይም መቃብር የሚነካ ሰባት ቀን ርኩስ ይሆናል።

参见章节 复制




ዘኍል 19:16
12 交叉引用  

እናንተ የቤተ መቅደስን ንዋያተ ቅድሳት የተሸከማችሁ! ከባቢሎን ውጡ፤ ከእርሱም ተለዩ፤ ርኩስ የሆነውን ነገር አትንኩ፤ ከመካከልዋም ወጥታችሁ ራሳችሁን አንጹ።


ይህን ካደረገ ግን ከነጻም በኋላ እንኳ ሰባት ቀን መቈየት አለበት፤


እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ከሕዝቡ መካከል የሞተውን ሰው አስከሬን በመንካት ስለ ሞተ ሰው ማናቸውም ራሳቸውን እንዳያረክሱ የአሮን ተወላጆች ለሆኑ ካህናት ንገራቸው፤


“የማንኛውንም ሰው አስከሬን የሚነካ ለሰባት ቀን ያልነጻ ሆኖ ይቈያል፤


በድንኳኑ ውስጥ የሚገኝ ክዳን የሌለው ማንኛውም እንስራም ሆነ ማሰሮ የረከሰ ይሆናል።


ከእናንተ መካከል ሰው የገደለ ወይም ሬሳ የነካ ሁሉ ለሰባት ቀን ከሰፈር ውጪ ይቈይ፤ በሦስተኛውና በሰባተኛው ቀን ራሳችሁንና የማረካችኋቸውን ሴቶች አንጹ።


“የሥጋ ደዌ በሽታ ያለበትን፥ ወይም ከሰውነቱ ፈሳሽ የሚወጣውንና ሬሳ በመንካት የረከሰውን ሰው ሁሉ ከሰፈር ያወጡ ዘንድ እስራኤላውያንን እዘዝ፤


በናዝራዊነት በአለበት ጊዜ ሁሉ ወደ ሞተ ሰው በድን አይቅረብ፤


ነገር ግን በድን ከመንካታቸው የተነሣ ያልነጹ ጥቂት ሰዎች ስለ ነበሩ በዚያን ቀን የፋሲካን በዓል ማክበር አልቻሉም፤ ስለዚህ እነርሱ ወደ ሙሴና አሮን ዘንድ ቀርበው እንዲህ አሉ፤


“እናንተ ግብዞች የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን! ወዮላችሁ! በውስጣቸው በሞቱ ሰዎች አጥንትና በርኩስ ነገር ሁሉ የተሞሉ፥ በውጪ ግን በኖራ ተለስነው የሚያምሩ መቃብሮችን ትመስላላችሁ።


ሰዎች ሳያውቁ በላዩ የሚሄዱበትን ምልክት የሌለውን መቃብር ስለምትመስሉ ወዮላችሁ!”


跟着我们:

广告


广告