Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘኍል 16:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ስለዚህም እያንዳንዳቸው ጥናቸውን ይዘው የእሳት ፍምና ዕጣን በመጨመር በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ከሙሴና ከአሮን ጋር ቆሙ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 እያንዳንዱ ሰው ጥናውን በመያዝ ፍም አድርጎበት፣ ዕጣን ጨምሮበት ከሙሴና ከአሮን ጋራ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ቆመ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 እያንዳንዳቸውም ጥናቸውን ወሰዱ፥ እሳትም አደረጉባቸው፥ ዕጣንም ጨመሩባቸው፥ ከሙሴና ከአሮንም ጋር በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ቆሙ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ጥና​ውን ወሰደ፤ እሳ​ትም አደ​ረ​ገ​በት፤ ዕጣ​ንም ጨመ​ረ​በት፤ ሙሴና አሮ​ንም በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ቆሙ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 እያንዳንዱም ጥናውን ወሰደ፥ እሳትም አደረገበት፥ ዕጣንም ጨመረበት፥ ከሙሴና ከአሮንም ጋር በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ቆመ።

参见章节 复制




ዘኍል 16:18
7 交叉引用  

ንጉሥ ዖዝያ መንግሥቱን ባጠናከረ ጊዜ ዕብሪተኛ ሆነ፤ ይህም ዕብሪተኛነቱ ወደ ውድቀት አደረሰው፤ በዕጣን መሠዊያው ላይ ዕጣን ለማጠን ወደ ቤተ መቅደስ በድፍረት በመግባቱ እግዚአብሔርን አሳዘነ፤


ከመሠዊያው የሚቃጠል የእሳት ፍም በጥናው ሞልቶም ሁለት እፍኝ ጣፋጭ ሽታ ያለውን የተወቀጠ ደቃቅ ዕጣን በመውሰድ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ያግባ፤


እዚያም በእግዚአብሔር ፊት በእሳቱ ላይ ዕጣን ይጨምርበት፤ እርሱም አይቶ እንዳይሞት የዕጣኑ ጢስ የስርየት መክደኛውን ይሸፍነው።


እያንዳንዳችሁ ጥናችሁን ይዛችሁ ኑ፤ በውስጡም ዕጣን ጨምሩበት፤ ከሁለት መቶ ኀምሳ ጥናዎች ጋር ወደ እግዚአብሔር ፊት ዕጣናችሁን ታቀርባላችሁ፤ አንተና አሮንም ዕጣናችሁን ታቀርባላችሁ።”


ከዚያም በኋላ ቆሬ መላውን ማኅበር በአንድነት ሰበሰበ፤ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ መጥተው በሙሴና በአሮን ፊት ለፊት ቆሙ፤ የእግዚአብሔርም ክብር ለመላው ማኅበር በድንገት ታየ።


“የአሮን ልጅ አልዓዛር ከነሐስ የተሠሩትን ጥናዎች ከተቃጠሉት ሰዎች ዘንድ እንዲወስድና ጥናዎቹ የተቀደሱ ስለ ሆኑ በውስጣቸው ያለውን ፍም ወደ ሌላ ስፍራ እንዲያፈስ ንገረው፤


በዚህም መቅሠፍቱ እንዲቆም አደረገ፤ አሮንም በሞቱትና በሕይወት ባሉት መካከል ቆሞ ነበር።


跟着我们:

广告


广告