ዘኍል 10:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 “በአገራችሁ ላይ ጦርነት አንሥቶ አደጋ የጣለባችሁን ጠላት ለመከላከል ስትሄዱ በእኔ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ዘንድ እንድትታወሱ በመለከቶቻችሁ የማስጠንቀቂያ ድምፅ ንፉ፤ እኔ አምላካችሁም አድናችኋለሁ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም9 በገዛ ምድራችሁ በግፍ በመጣባችሁ ጠላት ላይ ስትዘምቱ መለከቶቹን ከፍ ባለ ድምፅ ንፉ፤ በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ትታሰባላችሁ፤ ከጠላታችሁም እጅ ትድናላችሁ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 በሚቃወማችሁም ጠላት ላይ በምድራችሁ ወደ ጦርነት ስትወጡ ከፍ ባለ ድምፅ ማስጠንቀቂያውን በመለከቶቹ ንፉ፤ በጌታም በአምላካችሁ ፊት ትታወሳላችሁ፥ ከጠላቶቻችሁም ትድናላችሁ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 በሚገፋችሁም ጠላት ላይ በምድራችሁ ወደ ሰልፍ ስትወጡ በምልክት መለከቶችን ንፉ፤ በእግዚአብሔርም በአምላካችሁ ፊት ትታሰባላችሁ፤ ከጠላቶቻችሁም ትድናላችሁ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 በሚገፋችሁም ጠላት ላይ በምድራችሁ ወደ ሰልፍ ስትወጡ ከፍ ባለ ድምፅ መለከቶቹን ንፉ፤ በእግዚአብሔርም በአምላካችሁ ፊት ትታሰባላችሁ፥ ከጠላቶቻችሁም ትድናላችሁ። 参见章节 |