ነህምያ 8:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 ዕዝራ ከሕዝቡ ከፍ ብሎ በተሠራው መድረክ ላይ በቆመ ጊዜ፥ ሁሉም ትኲር ብለው ይመለከቱት ነበር፤ እርሱም የሕጉን መጽሐፍ በከፈተ ጊዜ፥ ሁሉም ከተቀመጡበት ተነሡ፤ 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም5 ዕዝራም መጽሐፉን ከፈተ፤ ከሕዝቡ ከፍ ብሎ ቆሞ ስለ ነበረ፣ ሁሉም ያዩት ነበረ፣ በከፈተውም ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ ቆሙ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 ዕዝራም ከሕዝቡ ሁሉ በላይ ከፍ ብሎ ነበርና በሕዝቡ ሁሉ ዐይን ፊት መጽሐፉን ከፈተ፤ በከፈተውም ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ ቆሙ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 ዕዝራም የሕዝቡ ሁሉ የበላይ ነበረና በሕዝቡ ሁሉ ፊት መጽሐፉን ገለጠ፤ በገለጠውም ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ ቆሙ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 ዕዝራም በሕዝቡ ሁሉ ላይ ከፍ ብሎ ሕዝቡ ሁሉ እያዩ መጽሐፉን ገለጠ በገለጠውም ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ ቆሙ። 参见章节 |