Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ነህምያ 8:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 በማግስቱ የጐሣ አለቆች ከካህናቱና ከሌዋውያኑ ጋር በአንድነት ሆነው የሕጉን ቃላት ትምህርት ለማጥናት ወደ ዕዝራ ዘንድ ሄዱ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ከወሩም በሁለተኛው ቀን የየቤተ ሰቡ ሁሉ ኀላፊዎች፣ የሕጉን ቃል ለመማር ከካህናቱና ከሌዋውያኑ ጋራ በጸሓፊው በዕዝራ ዙሪያ ተሰበሰቡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 በሁለተኛው ቀን ከሕዝቡ ሁሉ አለቆች የሆኑ አባቶች፥ ካህናቱ፥ ሌዋውያኑም የሕጉን ቃል እንዲተረጉምላቸው ወደ ጸሐፊው ወደ ዕዝራ ተሰበሰቡ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ቀን ከሕ​ዝቡ ሁሉ የአ​ባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች፥ ካህ​ና​ቱም፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑም የሕ​ጉን ቃል ይተ​ረ​ጕ​ም​ላ​ቸው ዘንድ ወደ ጸሓ​ፊው ወደ ዕዝራ ተሰ​በ​ሰቡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 በሁለተኛውም ቀን ከሕዝቡ ሁሉ የአባቶች ቤቶች አለቆች ካህናቱም ሌዋውያኑም የሕጉን ቃል ይተረጉምላቸው ዘንድ ወደ ጸሐፊው ወደ ዕዝራ ተሰበሰቡ።

参见章节 复制




ነህምያ 8:13
13 交叉引用  

በተጨማሪ ለሰባት ቀን በዓል እንዲያደርጉ በአንድነት ወስነው በዓሉን በደስታ አከበሩ።


የተነበበላቸውን ቃል ትርጒም በሚገባ ተረድተው ስለ ነበር ሕዝቡ ሁሉ ወደየቤታቸው ሄደው በመብላትና በመጠጣት እጅግ ተደሰቱ፤ ያላቸውንም ምግብ ከሌሎቹ ጋር አብረው ተካፈሉ፤


እስራኤላውያን ሕጉን በሚያነቡበት ጊዜ የሰባተኛውን ወር በዓል በዳስ ውስጥ ሆነው እንዲያከብሩ መታዘዙን እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት ባዘዘው ሕግ ውስጥ ተጽፎ አገኙ።


ዕውቀትን የሚወድ ሰው ከስሕተት መታረምን ይወዳል፤ ተግሣጽን የሚጠላ ግን ጅል ሰው ነው።


እነርሱም እርስ በርሳቸው “በመንገድ ሳለን ሲነግረንና ቅዱሳት መጻሕፍትንም እየጠቀሰ ሲያስረዳን ልባችን እንደ እሳት ይቃጠል አልነበረምን?” ተባባሉ።


ጳውሎስና በርናባስ ከምኲራብ ሲወጡ ይህንኑ ነገር በሚመጣው ሰንበት እንደገና እንዲነግሩአቸው ሰዎቹ ለመኑአቸው።


ጴጥሮስና ዮሐንስ ለሕዝቡ ሲናገሩ ሳሉ ካህናትና የቤተ መቅደሱ የዘበኞች አለቃ እንዲሁም ሰዱቃውያን ወደ እነርሱ መጡና


跟着我们:

广告


广告