ነህምያ 5:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 ሌሎቹ ደግሞ “ከደረሰብን ብርቱ ራብ ሕይወታችንን ለማትረፍ የሚያስችል እህል ለማግኘት ስንል እርሻችንን፥ የወይን ተክላችንንና ቤታችንን ሁሉ መያዣ አድርገን እስከ መስጠት ደርሰናል” ይሉ ነበር። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም3 ሌሎቹ፣ “በራቡ ወቅት እህል ለማግኘት ስንል ዕርሻችንን፣ የወይን ተክል ቦታችንንና ቤታችንን እስከ ማስያዝ ደርሰናል” አሉ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 እንዲህ የሚሉም ነበሩ፦ “በራቡ ጊዜ እህል እንድንወስድ እርሻችን፥ የወይን ቦታችንንና ቤታችንን አስይዘናል” 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 “ከራብ የተነሣም እህልን እንሸምት ዘንድ እርሻችንንና ወይናችንን፥ ቤታችንንም አስይዘናል” የሚሉ ነበሩ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)3 አያሌዎቹም፦ ከራብ የተነሣ እህልን እንሸምት ዘንድ እርሻችንና ወይናችንን ቤታችንንም አስይዘናል ይሉ ነበር። 参见章节 |