Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ነህምያ 3:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ወርቅ አንጣሪው የሐርሃያ ልጅ ዑዝኤል ከዚያ ቀጥሎ ያለውን ክፍል ሠራ። ቀጥሎ ያለውንም ክፍል ሽቶ ቀማሚው ሐናንያ ሠራ፤ እነዚህ ሰዎች ኢየሩሳሌምን “ሰፊው ቅጽር” ተብሎ እስከሚጠራው ስፍራ ድረስ ያለውን ሁሉ ሠሩ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ከወርቅ አንጥረኞች አንዱ የሆነው የሐርሃያ ልጅ ዑዝኤል የሚቀጥለውን ክፍል ሠራ፤ ከሽቱ ቀማሚዎች አንዱ የሆነው ሐናንያ ደግሞ ከዚያ ቀጥሎ ያለውን መልሶ ሠራ። እነርሱም ሰፊው ቅጥር ተብሎ እስከሚጠራው ድረስ ኢየሩሳሌምን መልሰው ሠሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 በአጠገባቸውም ወርቅ አንጥረኛው የሐርሃያ ልጅ ዑዚኤል አደሰ። በአጠገቡም የሽቶ ቀማሚዎች ልጅ ሐናንያ አደሰ፤ እስከ ሰፊው ቅጥር ድረስ ኢየሩሳሌምን አደሱ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸ​ውም ወርቅ አን​ጥ​ረ​ኛው የሐ​ሬ​ህያ ልጅ ዑዝ​ኤል ሠራ። በአ​ጠ​ገ​ቡም ከሽቱ ቀማ​ሚ​ዎች የነ​በረ ሐና​ንያ ሠራ፤ እስከ ሰፊው ቅጥር ድረስ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ጠገኑ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 በአጠገባቸውም ወርቅ አንጥረኛው የሐርሃያ ልጅ ዑዝኤል አደሰ። በአጠገቡም ከሽቱ ቀማሚዎች የነበረ ሐናንያ አደሰ፥ እስከ ሰፊው ቅጥር ድረስ ኢየሩሳሌምን ጠገኑ።

参见章节 复制




ነህምያ 3:8
6 交叉引用  

ከዚህ በኋላ ዮሴፍ አገልጋዮቹ የሆኑትን መድኃኒት ቀማሚዎች የአባቱን ሬሳ መልካም መዓዛ ባለው ሽቶ እያሹ እንዲያደርቁት ትእዛዝ ሰጠ።


ሌላው የመዘምራን ቡድን ሰልፍ የቅጽሩን ግንብ ጫፍ በመከተል ወደ ግራ በኩል አለፈ፤ እኔም ከሕዝቡ እኩሌታ ጋር ይህንኑ የቡድን ሰልፍ እከተል ነበር፤ የእቶኑንም ግንብ አልፈን ወደ ሰፊው ቅጽር ግንብ ደረስን።


እንደ ሽቶ ቀላቅለህ የተቀደሰ የቅባት ዘይት ሥራ፤


የሞቱ ዝንቦች ተቀምሞ የተሠራውን የዘይት ሽቶ ሊያገሙት ይችላሉ፤ እንዲሁም ትንሽ ሞኝነት ታላቅ ጥበብን ያጠፋል።


አንዳንድ ሰዎች ኰረጆአቸውን ከፍተው ወርቅ እንደ ልባቸው ይመዛሉ፤ ብሩንም በሚዛን ይመዝናሉ፤ ጣዖት አድርጎ እንዲሠራላቸውም አንጥረኛ ይቀጥራሉ፤ ከተሠራም በኋላ እየሰገዱ ያመልኩታል።


跟着我们:

广告


广告