Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ነህምያ 3:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 የምጽጳ ወረዳ ገዥ የሆነው የኢያሱ ልጅ ዔዜር በጦር መሣሪያው ግምጃ ቤት ፊት ለፊት ያለውን እስከ ቅጽሩ መመለሻ ማእዘን ድረስ ያለውን ሁሉ ሠራ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ከርሱም ቀጥሎ ወደ ጦር መሣሪያ ግምጃ ቤት በሚያወጣውና እስከ ማእዘኑ በሚደርሰው ትይዩ ያለውን ሌላ ክፍል የምጽጳ ገዥ የኢያሱ ልጅ ኤጽር መልሶ ሠራ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 በአጠገቡ የሚጽጳ ገዢ የኢያሱ ልጅ ዔዜር በግንቡ መደገፊያ ወደ ጦር መሣሪያ ግምጃ ቤት መወጣጫ ፊት ለፊት ያለውን ሁለተኛውን ክፍል አደሰ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 በአ​ጠ​ገ​ቡም የመ​ሴፋ ገዢ የኢ​ያሱ ልጅ አዙር በማ​ዕ​ዘኑ አጠ​ገብ በመ​ወ​ጣ​ጫው ግንብ አን​ጻር ያለ​ውን ሌላ​ውን ክፍል ሠራ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 በአጠገቡም የምጽጳ አለቃ የኢያሱ ልጅ ኤጽር በማዕዘኑ አጠገብ በጦር መሣሪያ ቤት አንጻር ሌላውን ክፍል አደሰ።

参见章节 复制




ነህምያ 3:19
6 交叉引用  

ዖዝያ በማእዘን ቅጽር በር፥ በሸለቆ ቅጽር በርና በቅጽሩም መጠምዘዣ ላይ መቈጣጠሪያ ግንቦችን በመሥራት የኢየሩሳሌምን ምሽጎች አጠናከረ፤


ከሌዋውያን ወገን፦ የአዛንያ ልጅ ኢያሱ፥ የሔናዳድ ጐሣ የሆነው ቢኑይ፥ ቃድሚኤል፥ ሸባንያ፥ ሆዲያ፥ ቀሊጣ፥ ፐላያ፥ ሐናን፥ ሚካ፥ ረሖብ፥ ሐሻብያ፥ ዛኩር፥ ሼሬብያ፥ ሸባንያ፥ ሆዲያ፥ ባኒና በኒኑ።


ሌዋውያን፦ የምስጋና መዝሙር ኀላፊዎች የነበሩት ሌዋውያን ኢያሱ፥ ቢኑይ፥ ቃድሚኤል፥ ሼሬብያ፥ ይሁዳና ማታንያ ነበሩ።


የምጽጳ ወረዳ ገዢ የሆነው የኮልሖዜ ልጅ ሻሉም የምንጩን ቅጽር በር እንደገና ሠራ፤ ክዳን ከሠራለትም በኋላ መዝጊያዎችን አቆመ፤ ለበሮቹም ቊልፎችንና መወርወሪያዎችን አበጀ፤ በሼላሕ ኩሬ ቅጥር በኩል ከቤተ መንግሥቱ የአትክልት ቦታ ጀምሮ ከዳዊት ከተማ ወደታች እስከሚያወርደው ደረጃ ድረስ ያለውን ክፍል እንደገና ሠራ።


ከዚያም ቀጥሎ ያለውን ክፍል የሌላው የቀዒላ ወረዳ እኩሌታ ገዢ የሆነው የሔናዳድ ልጅ ባዋይ ሠራው።


የሔናዳድ ልጅ ቢኑይ ከዐዛርያ ቤት አንሥቶ እስከ ቅጽሩ ማእዘን ያለውን ሠራ።


跟着我们:

广告


广告