ነህምያ 2:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም16 በሀገሪቱ ከነበሩትም ባለሥልጣኖች መካከል የት እንደ ነበርኩና ምን እንዳደረግሁ ያወቀ ማንም አልነበረም፤ ከዚህም በቀር ከአይሁድ ጓደኞቼ ይኸውም ከካህናቱ፥ ከመሪዎቹም ሆነ ከባለሥልጣኖቹ ወይም የሥራው ተካፋዮች ከሚሆኑት ሌሎች ሰዎች ለአንዱም እንኳ የነገርኩት ምንም ነገር አልነበረም። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም16 ለአይሁድ ወይም ለካህናቱ ወይም ለመኳንንቱ ወይም ለሹማምቱ ወይም ሥራውን ለሚሠሩት ሰዎች ገና ምንም የተናገርሁት ነገር ስላልነበረ፣ ወዴት እንደ ሄድሁ ወይም ምን እንዳደረግሁ ሹማምቱ አላወቁም። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)16 ለአይሁድ ወይም ለካህናቱ ወይም ለታላላቆች ወይም ለሹማምቱ ወይም ሥራ ይሠሩ ለነበሩት ለሌሎች ስላልተናገርኩ፥ ሹማምንቱ ወዴት እንደ ሄድኩ ወይም ምን እንዳደረግሁ አላወቁም። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)16 ጠባቆች ግን ወዴት እንደ ሄድሁ፥ ምን እንዳደረግሁም አላወቁም ነበር፤ ለአይሁድና ለካህናቱ፥ ለታላላቆችና ለሹሞቹም፥ ሥራም ይሠሩ ለነበሩት ለሌሎች እስከዚያ ጊዜ ገና አልተናገርሁም ነበር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)16 ሹማምቱ ግን ወዴት እንደ ሄድሁ፥ ምን እንዳደረግሁም አላወቁም ነበር፤ ለአይሁድና ለካህናቱ፥ ለታላላቆችና ለሹማምቱም፥ ሥራም ይሠሩ ለነበሩት ለሌሎች ገና አልተናገርሁም ነበር። 参见章节 |