ነህምያ 12:43 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም43 በዚያም ዕለት ብዙ መሥዋዕት ቀረበ፤ ሕዝቡም እግዚአብሔር ደስ ስላሰኛቸው ታላቅ ሐሴት አደረጉ፤ ሴቶችም፥ ልጆችም አብረው ተደስተዋል፤ በኢየሩሳሌም የነበረው የእልልታቸው ድምፅ እስከ ሩቅ ድረስ ይሰማ ነበር። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም43 እግዚአብሔር ታላቅ ደስታ ስለ ሰጣቸው፣ በዚያች ዕለት ደስ ብሏቸው ብዙ መሥዋዕት አቀረቡ፤ ሴቶችና ልጆችም እንደዚሁ ደስ አላቸው፤ ከዚህም የተነሣ በኢየሩሳሌም የነበረው የደስታ ድምፅ እስከ ሩቅ ድረስ ይሰማ ነበር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)43 እግዚአብሔር በታላቅ ደስታ ደስ አሰኝቶአቸዋልና በዚያ ቀን ትልቅ መሥዋዕት አቀረቡ፥ ደስም አላቸው፤ ሴቶቹና ልጆቹም ደግሞ ደስ አላቸው፤ የኢየሩሳሌምም ደስታ ከሩቅ ተሰማ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)43 እግዚአብሔርም በታላቅ ደስታ ደስ አሰኝቶአቸዋልና በዚያ ቀን ትልቅ መሥዋዕት አቀረቡ፤ ደስም አላቸው፤ ሴቶቹና ልጆቹም ደግሞ ደስ አላቸው፤ ደስታቸውም በኢየሩሳሌም ከሩቅ ተሰማ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)43 እግዚአብሔርም በታላቅ ደስታ ደስ አሰኝቶአቸዋልና በዚያ ቀን ትልቅ መሥዋዕት አቀረቡ፥ ደስም አላቸው፥ ሴቶቹና ልጆቹም ደግሞ ደስ አላቸው፥ የኢየሩሳሌምም ደስታ ከሩቅ ተሰማ። 参见章节 |