Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ነህምያ 11:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 በኢየሩሳሌም የሌዋውያን አለቃ ዑዚ የባሂ ልጅ፥ የሖሻብያ ልጅ፥ የማታንያ ልጅ፥ የሚካ ልጅ ነበር። ዑዚ የቤተ መቅደስ መዘምራን ኀላፊ የነበረው የአሳፍ ዘር ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 በኢየሩሳሌም የሌዋውያኑ ዋና አለቃ የሚካ ልጅ፣ የመታንያ ልጅ፣ የሐሸብያ ልጅ፣ የባኒ ልጅ ኦዚ ነበረ፤ ኦዚ በእግዚአብሔር ቤት አገልግሎት ለሚዘመረው መዝሙር ኀላፊ ከነበሩት ከአሳፍ ዘሮች አንዱ ነበረ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 በእግዚአብሔር ቤት ሥራ ላይ ከነበሩ መዘምራን ከአሳፍ ልጆች ወገን የሚካ ልጅ፥ የማታንያ ልጅ፥ የሓሻብያ ልጅ፥ የባኒ ልጅ ዑዚ በኢየሩሳሌም የሌዋውያን አለቃ ነበረ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ሥራ ላይ ከነ​በሩ መዘ​ም​ራን ከአ​ሳፍ ልጆች ወገን የሚካ ልጅ፥ የመ​ታ​ንያ ልጅ፥ የሐ​ሳ​ብያ ልጅ፥ የባኒ ልጅ ኦዚ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የሌ​ዋ​ው​ያን አለቃ ነበረ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 በእግዚአብሔርም ቤት ሥራ ላይ ከነበሩ መዘምራን ከአሳፍ ልጆች ወገን የሚካ ልጅ የመታንያ ልጅ የሐሸብያ ልጅ የባኒ ልጅ አዚ በኢየሩሳሌም የሌዋውያን አለቃ ነበረ።

参见章节 复制




ነህምያ 11:22
19 交叉引用  

መፊቦሼት ሚካ የተባለ ወጣት ልጅ ነበረው፤ የጺባ ቤተሰብ አባሎች በሙሉ የመፊቦሼት አገልጋዮች ሆኑ፤


እንዲሁም ከመራሪ ጐሣ የሆኑትን ሐሻብያና የሻዕያ ተብለው የሚጠሩትን ሰዎች ቊጥራቸው ኻያ ከሆነ ዘመዶቻቸው ጋር ላኩልን።


ሠራያ፥ የሒልቅያ ልጅ፥ የመሹላም ልጅ፥ የጻዶቅ ልጅ፥ የመራዮት ልጅ፥ የእግዚአብሔር ቤት አለቃ የነበረው የአሒጡብ ልጅ፥


የእርሱም ወንድሞች ስመጥር ወታደሮች የሆኑት አባላት ብዛት 128 ነበር፤ መሪያቸውም ዛብድኤል ተብሎ የሚጠራ የሐጌዶሊም ልጅ ነበር።


የዚክሪ ልጅ ኢዩኤል መሪያቸው ሲሆን፥ የሀስኑአ ልጅ ይሁዳ በማዕርግ ሁለተኛ የሆነ የከተማይቱ ባለሥልጣን ነበር።


እነርሱንም ደግሞ መዕሤያ፥ ሸማዕያ፥ አልዓዛር፥ ዑዚ፥ የሆሐናን፥ ማልኪያ፥ ኤላምና ኤዜር ተከትለዋቸው ይጓዙ ነበር፤ እንደ ቆምንም መዘምራኑ በይዝራሕያ እየተመሩ ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ ዘመሩ።


ከንጉሥ ዳዊትና የመዘምራን አለቃ ከነበረው አሳፍ ዘመንም ጀምሮ ለመዘምራንና ለማኅሌታዊ ዜማ መሪዎች ነበሩአቸው።


ለዕቃ ግምጃ ቤቱም ኀላፊነት ካህኑን ሼሌምያን፥ የሕግ ምሁሩን ሳዶቅንና ሌዋዊውን ፐዳያን መደብሁ፤ የማታንያ የልጅ ልጅ የሆነው የዛኩር ልጅ ሐናንም የእነርሱ ረዳት ነበር፤ እነዚህም ሰዎች ለሥራ ጓደኞቻቸው የሚሆነውን መተዳደሪያ ለማከፋፈል ታማኞች ነበሩ።


በቅጽሩ ሥራ ተካፋዮች የነበሩት ሌዋውያን ስም ዝርዝር ከዚህ የሚከተለው ነው፦ የባኒ ልጅ ረሑም ከዚያ ቀጥሎ ያለውን ክፍል ሠራ። የቀዒላ ወረዳ እኩሌታ ገዢ የሆነው ሐሻብያ ወረዳውን በመወከል ቀጥሎ ያለውን ክፍል ሠራ።


ከዚህ በኋላ ተነሥተው ባሉበት ስፍራ ቆሙ፤ ከዚህ ቀጥሎ ስማቸው የተዘረዘረ ሌዋውያንም የሕጉን መጽሐፍ ትርጒም ለሕዝቡ አብራሩላቸው፤ እነርሱም ኢያሱ፥ ባኒ፥ ሼሬብያ፥ ያሚን፥ ዓቁብ፥ ሻበታይ፥ ሆዲያ፥ መዕሤያ፥ ቀሊጣ፥ ዐዛርያስ፥ ዮዛባድ፥ ሐናንና ፐላያ ነበሩ።


መንፈስ ቅዱስ እናንተን ኤጲስ ቆጶሳት አድርጎ ሾሞአችኋል፤ እንግዲህ ለራሳችሁና ለመንጋው ተጠንቀቁ፤ እግዚአብሔር በገዛ ልጁ ደም የዋጃትን ቤተ ክርስቲያን ጠብቁ።


跟着我们:

广告


广告