ነህምያ 10:34 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም34 በሕጉ ስለ መሥዋዕት በተጻፈው መሠረት ለአምላካችን ለእግዚአብሔር የሚቀርበው መሥዋዕት የሚቃጠልበትን የማገዶ እንጨት የትኞቹ ጐሣዎች ማቅረብ እንደሚገባቸው እኛ ሕዝቡ፥ ካህናቱና ሌዋውያኑ በየዓመቱ ዕጣ በማውጣት እንወስናለን። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም34 “እኛ፣ ማለት ካህናቱ፣ ሌዋውያኑና ሕዝቡ በየዓመቱ በተወሰነው ጊዜ በሕጉ እንደ ተጻፈው፣ በአምላካችን በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ የሚነድደውን ዕንጨት የእያንዳንዳችን ቤተ ሰብ መቼ ወደ አምላካችን ቤት ማምጣት እንዳለበት ለመወሰን ዕጣ ተጣጣልን። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)34 እኛም፥ ካህናቱና ሌዋውያኑ ሕዝቡም፥ እንደ አባቶቻችን ቤቶች በተወሰነ ጊዜ በየዓመቱ ወደ አምላካችን ቤት አምጥተን በሕጉ እንደ ተጻፈ በአምላካችን በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ ይቃጠል ዘንድ ስለ እንጨት ቁርባን ዕጣ ተጣጣልን፥ 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)34 እኛም ካህናቱና ሌዋውያኑ ሕዝቡም፥ እንደ አባቶቻችን ቤቶች በተወሰነ ጊዜ በየዓመቱ ወደ አምላካችን ቤት አምጥተን በሕጉ እንደ ተጻፈ በአምላካችን በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ ይቃጠል ዘንድ ስለ ዕንጨት ቍርባን ዕጣ ተጣጣልን፤ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)34 እኛም፥ ካህናቱና ሌዋውያኑ ሕዝቡም፥ እንደ አባቶቻችን ቤቶች በተወሰነ ጊዜ በየዓመቱ ወደ አምላካችን ቤት አምጥተን በሕጉ እንደ ተጻፈ በአምላካችን በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ ይቃጠል ዘንድ ስለ እንጨት ቁርባን ዕጣ ተጣጣልን፥ 参见章节 |
ኻያ አራቱ የቤተሰብ ቡድኖች በዕጣ የወጣላቸው የሥራ ምድቡ ክፍፍል ቅደም ተከተል ተራ እንደሚከተለው ነው፦ አንደኛ በይሆያሪብ የሚመራው ቡድን፥ ሁለተኛ በይዳዕያ የሚመራው ቡድን፥ ሦስተኛ በሐሪም የሚመራው ቡድን፥ አራተኛ በሰዖሪም የሚመራው ቡድን፥ አምስተኛ በማልኪያ የሚመራው ቡድን፥ ስድስተኛ በሚያሚን የሚመራው ቡድን፥ ሰባተኛ በሀቆጽ የሚመራው ቡድን፥ ስምንተኛ በአቢያ የሚመራው ቡድን፥ ዘጠነኛ በኢያሱ የሚመራው ቡድን፥ ዐሥረኛ በሸካንያ የሚመራው ቡድን፥ ዐሥራ አንደኛ በኤልያሺብ የሚመራው ቡድን፥ ዐሥራ ሁለተኛ በያቂም የሚመራው ቡድን፥ ዐሥራ ሦስተኛ በሑፓ የሚመራው ቡድን፥ ዐሥራ አራተኛ በዬሼብአብ የሚመራው ቡድን፥ ዐሥራ አምስተኛ በቢልጋ የሚመራው ቡድን፥ ዐሥራ ስድስተኛ በኢሜር የሚመራው ቡድን፥ ዐሥራ ሰባተኛ በሔዚር የሚመራው ቡድን፥ ዐሥራ ስምንተኛ በሃፒጼጽ የሚመራው ቡድን፥ ዐሥራ ዘጠነኛ በፐታሕያ የሚመራው ቡድን፥ ኻያኛ በይሔዝቄል የሚመራው ቡድን፥ ኻያ አንደኛ በያኪን የሚመራው ቡድን፥ ኻያ ሁለተኛ በጋሙል የሚመራው ቡድን፥ ኻያ ሦስተኛ በደላያ የሚመራው ቡድን፥ ኻያ አራተኛ በማዓዝያ የሚመራው ቡድን።