Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ናሆም 1:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 የነነዌ ሕዝብ ሆይ! በእግዚአብሔር ላይ ሤራ የሚያሤርና ክፉ ምክር የሚመክር ሰው ከመካከላችሁ ተነሥቶአል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ነነዌ ሆይ፤ በእግዚአብሔር ላይ የሚያሤር፣ ምናምንቴ ክፉ መካሪ፣ ከአንቺ ዘንድ ወጥቷል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 በጌታ ላይ ክፉ ነገር የሚያሤር፥ ክፋትንም የሚመክር፥ ከአንቺ ዘንድ ወጥቶአል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 በእግዚአብሔር ላይ በክፉ የሚያስብ፥ ክፋትን የሚመክር፥ ከአንተ ዘንድ ወጥቶአል።

参见章节 复制




ናሆም 1:11
11 交叉引用  

በዚያን ጊዜ ሼባዕ ተብሎ የሚጠራ ጠባዩ የተበላሸ የማይረባ አንድ ሰው በጌልገላ ይኖር ነበር፤ እርሱም ትውልዱ ከብንያም ነገድ ሲሆን አባቱ ቢክሪ ይባላል፤ ይህም ሼባዕ እምቢልታ ነፍቶ “ከዳዊት ጋር ምንም ድርሻ የለንም! ከእሴይ ልጅ ጋር ምንም ዕድል ፈንታ የለንም! የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! እያንዳንድህ ወደ ቤትህ ግባ!” ሲል ድምፁን ከፍ አድርጎ ተናገረ።


ሕዝቅያስ ‘በእግዚአብሔር ታመኑ፤ እርሱ ያድናችኋል፤ ከተማችንም በአሦርያውያን ሠራዊት እጅ እንዳትገባ ይከላከልልናል’ እያለ የሚሰብካችሁን አትስሙ፤


ዘግየት ብሎም ኢዮርብዓም የማይረቡ ወሮበሎችን ሰበሰበ፤ እነርሱም በዕድሜው ማነስና በዕውቀት ያልበሰለ በመሆኑ ሊቋቋማቸው የማይችለውን የሰሎሞንን ልጅ ሮብዓምን በረቱበት።


እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ! እነዚህ ሰዎች መጥፎ ዕቅድ ያወጣሉ፤ በዚህችም ከተማ ክፉ ምክር ይመክራሉ፤


ክፉ ሥራ ለመሥራት ለሚያቅዱና በመኝታቸው ሳሉ ተንኰል ለሚያውጠነጥኑ ወዮላቸው! ያን ለማድረግ ሥልጣን ስላላቸው ሌሊቱ ሲነጋ ዕቅዳቸውን በሥራ ላይ ያውሉታል።


እናንተ በእግዚአብሔር ላይ የምታሤሩት ለምንድን ነው? እርሱ እናንተን እስከ መጨረሻው ይደመስሳችኋል፤ ዳግመኛም በእርሱ ላይ መነሣሣት ከቶ አትችሉም።


የዔሊ ልጆች ምንም የማይረቡ ስድ አደጎች ነበሩ፤ እግዚአብሔርንም አያከብሩም ነበር፤


跟着我们:

广告


广告