Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሚክያስ 5:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 መተታችሁን አጠፋለሁ፤ ሟርተኞችም ከእንግዲህ ወዲህ በመካከላችሁ አይገኙም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ጥንቈላችሁን አጠፋለሁ፤ ከእንግዲህም አታሟርቱም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 የተቀረጹ ምስሎችህንና ሐውልቶችህን ከመካከልህ አጠፋለሁ፥ ከእንግዲህም ወዲያ ለእጅህ ሥራ አትሰግድም፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 መተትንም ከእጅህ አጠፋለሁ፥ ምዋርተኞችም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆኑልህም፥

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 መተትንም ከእጅህ አጠፋለሁ፥ ምዋርተኞችም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆኑልህም፥

参见章节 复制




ሚክያስ 5:12
14 交叉引用  

ሰዎች ይሰግዱላቸው ዘንድ በእጃቸው የሠሩአቸውን የብርና የወርቅ ምስሎች ለፍልፈሎችና ለሌሊት ወፎች እየጣሉላቸው ይሄዳሉ።


እንግዲህ የያዕቆብ ልጆች እስራኤላውያን ለኃጢአታቸው ይቅርታ ማግኘት የሚችሉት የአሕዛብን የመሠዊያ ድንጋዮች እንደ ኖራ ፈጭተው፥ የዕጣን መሠዊያዎችንም ሆነ አሼራ ተብላ የምትጠራውን የሴት አምላክ ምስሎች ሲያስወግዱ ነው።


የቀረውንም ጒማጅ ጣዖት አድርጎ ይሠራና በፊቱ ተደፍቶ በመስገድ ያመልከዋል፤ “አንተ አምላኬ ነህ፤ አድነኝ!” እያለ ወደ እርሱ ይጸልያል።


ቤቶችሽን በእሳት ያቃጥላሉ፤ በብዙ ሴቶች ፊት ፍርድን ተግባራዊ ያደርጉብሻል፤ በዚህ ዐይነት አመንዝራነትሽንና ለወዳጆችሽ የዝሙት ዋጋ መክፈልሽን እንድትተዪ አደርግሻለሁ።


በእናንተ ላይ ንጹሕ ውሃ በመርጨት ከጣዖት አምልኮአችሁና ከርኲሰታችሁ ሁሉ እንድትነጹ አደርጋለሁ።


የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “በዚያን ጊዜ ለዳዊት ልጆችና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ከኃጢአታቸውና ከርኲሰታቸው የሚያነጻ ምንጭ ይከፈታል።


ከዚህ በኋላ ሙሴ እንዲህ አለ፦ “እነዚህ ሀገራቸውን አስለቅቀህ የምትወርስባቸው ሕዝቦች ሟርተኝነትንና ጥንቈላን ይወዳሉ፤ አንተ ግን እግዚአብሔር አምላክህ ይህን እንድታደርግ አይፈቅድም።


ነገር ግን አውሬው ተያዘ፤ ከእርሱም ጋር በፊቱ ብዙ ተአምራት ያደርግ የነበረው ሐሰተኛው ነቢይ ተያዘ፤ እርሱ የአውሬው ምልክት የነበረባቸውንና ለአውሬውም ምስል ይሰግዱ የነበሩትን ተአምራት እያደረገ ያስታቸው ነበር፤ እነዚህ ሁለቱ በዲን ወደሚቃጠለው የእሳት ባሕር ከነሕይወታቸው ተጣሉ።


እንደ ውሻ የሚልከፈከፉ፥ አስማተኞች፥ አመንዝሮች፥ ነፍሰ ገዳዮች፥ ጣዖት አምላኪዎች፥ ውሸትን የሚወዱና በሐሰት መንገድ የሚሄዱ ሁሉ ከከተማይቱ ውጪ ይሆናሉ።


跟着我们:

广告


广告