Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ማቴዎስ 5:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 እኔ ግን ‘ሴትን ተመልክቶ የተመኛት ሁሉ፥ ያን ጊዜ በልቡ ከእርስዋ ጋር አመነዘረ’ እላችኋለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 እኔ ግን እላችኋለሁ፤ ሴትን በምኞት ዐይን የተመለከተ ሁሉ በልቡ ከርሷ ጋራ አመንዝሯል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 እኔ ግን እላችኋለሁ፤ ወደ ሴት አይቶ የተመኛት ሁሉ ከወዲሁ በልቡ ከእርሷ ጋር አመንዝሮአል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 እኔ ግን እላችኋለሁ፤ ወደ ሴት ያየ ሁሉ የተመኛትም ያን ጊዜ በልቡ ከእርስዋ ጋር አመንዝሮአል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ወደ ሴት ያየ ሁሉ የተመኛትም ያን ጊዜ በልቡ ከእርስዋ ጋር አመንዝሮአል።

参见章节 复制




ማቴዎስ 5:28
20 交叉引用  

የአገሩ ገዢ የሒዋዊው የሐሞር ልጅ ሴኬም ባያት ጊዜ ያዛት፤ በማስገደድም ክብረ ንጽሕናዋን ደፈረ።


አንድ ቀን ከቀትር በኋላ ዘግየት ብሎ ዳዊት ከቀን እንቅልፉ ነቅቶ ወደ ቤተ መንግሥቱ ሰገነት ወጣ፤ እዚያም ወዲያና ወዲህ ሲመላለስ ገላዋን የምትታጠብ አንዲት ሴት አየ፤ ሴትዮዋም በጣም ውብ ነበረች፤


“ቈንጆይቱን በፍትወት ዐይን እንዳልመለከት፥ ከዐይኔ ጋር ቃል ኪዳን ገብቼአለሁ።


ልቤ በሌላ ሴት ፍቅር ተማርኮ እንደ ሆነ፥ የጐረቤቴንም ሚስት ለማግኘት በደጃፉ አድብቼ እንደ ሆነ፥


የሁሉም ነገር ፍጹምነት ወሰን አለው፤ የትእዛዞችህ ፍጹምነት ግን ወሰን የለውም።


“የሌላውን ሰው ቤት አትመኝ፤ ሚስቱን፥ አገልጋዮቹን፥ ከብቱን፥ አህዮቹንም ሆነ ማናቸውንም ንብረቱን ሁሉ አትመኝ።”


ቊንጅናዋን አትመኝ፤ በዐይንዋ ጥቅሻ አትማረክ።


ልክ እነርሱን ስታይ በፍትወት ተቃጥላ እነርሱ ወደሚኖሩባት ወደ ባቢሎን መልእክተኞችን ላከች፤


ከሌላ ሰው ሚስት ጋር በመተኛት ራስህን ከእርስዋ ጋር አታርክስ።


ክፉ ማሰብ፥ ሰው መግደል፥ ማመንዘር፥ ዝሙት ማድረግ፥ መስረቅ፥ በሐሰት መመስከር የሰውን ስም ማጥፋት፥ ይህ ሁሉ ከሰው ልብ ይወጣል።


እኔ ግን እላችኋለሁ፤ በወንድሙ ላይ የሚቈጣ ሁሉ ይፈረድበታል፤ ደግሞም ወንድሙን፥ ‘አንተ የማትረባ!’ ብሎ የሚሳደብ በሸንጎ ይፈረድበታል፤ ‘ደደብ!’ ብሎ የሚሳደብ ሁሉ በገሃነመ እሳት ይፈረድበታል።


እኔ ግን እንዲህ እላችኋለሁ፤ ክፉ የሚያደርግባችሁን ሰው አትበቀሉት። ነገር ግን ቀኝ ጒንጭህን ለሚመታህ፥ ግራ ጒንጭህን አዙርለት።


ሕግ መንፈሳዊ መሆኑን እናውቃለን። እኔ ግን የኃጢአት ባሪያ ለመሆን የተሸጥሁ ሥጋዊ ነኝ።


“አንድ ሰው ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ተኝቶ ቢገኝ ሁለቱም ይገደሉ። በዚህም ዐይነት ይህን ክፉ ነገር ከእስራኤል አስወግዱ።


ኃጢአት ከማድረግ የማይቈጠብ ቅንዝረኛ ዐይን አላቸው፤ የኃጢአት መሥራት ፍላጎታቸው መቼም አይረካም፤ በእምነት ጸንተው ያልቆሙትን ሰዎች ያታልላሉ፤ ለገንዘብ ይስገበገባሉ። የተረገሙ ሰዎች ናቸው።


በዓለም ያለው ሁሉ የሥጋ ምኞት፥ የዐይን አምሮት፥ የኑሮ ትምክሕት ከዓለም ነው እንጂ ከእግዚአብሔር አብ አይደለም።


跟着我们:

广告


广告