ማቴዎስ 2:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 ‘በይሁዳ ክፍለ ሀገር የምትገኚ አንቺ ቤተልሔም ሆይ! ሕዝቤን እስራኤልን የሚጠብቅ መሪ ከአንቺ ስለሚወጣ፥ ከይሁዳ ታላላቅ ከተሞች በምንም አታንሺም።’ ” 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም6 “ ‘በይሁዳ ምድር የምትገኚው አንቺ ቤተ ልሔም፣ ከሌሎቹ ከይሁዳ ገዦች በምንም አታንሺም፤ የሕዝቤ የእስራኤል ጠባቂ የሚሆን፣ ከአንቺ ይወጣልና።’ ” 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 “በይሁዳ ምድር የምትገኚ አንቺ ቤተልሔም፥ ከይሁዳ ገዢዎች ከቶ አታንሽም፤ ሕዝቤን እስራኤልን የሚጠብቅ መሪ ከአንቺ ይወጣልና።” 参见章节 |
ከምርኮ ከተመለሱትም ሰዎች መካከል በተለይ የቀድሞ አባቶቻቸው ከዚህ በሚከተሉት ከተሞች ይኖሩ የነበሩት ዝርዝር ይህ ነው፦ የቤተልሔም ተወላጆች 123 የነጦፋ ተወላጆች 56 የዐናቶት ተወላጆች 128 የዓዝማዌት ተወላጆች 42 የቂርያትይዓሪም፥ የከፊራና የበኤሮት ተወላጆች 743 የራማና የጌባዕ ተወላጆች 621 የሚክማስ ተወላጆች 122 የቤትኤልና የዐይ ተወላጆች 223 የነቦ ተወላጆች 52 የማግቢሽ ተወላጆች 156 የሌላይቱ ዔላም ተወላጆች 1254 የሓሪም ተወላጆች 320 የሎድ፥ የሐዲድና የኦኖ ተወላጆች 725 የኢያሪኮ ተወላጆች 345 የሰናአ ተወላጆች 3630