Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ማርቆስ 7:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ሙሴ፦ ‘አባትህንና እናትህን አክብር፤ ደግሞም በአባቱ ወይም በእናቱ ላይ ክፉ የሚናገር ሰው በሞት ይቀጣ፤’ ይላል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ሙሴ፣ ‘አባትህንና እናትህን አክብር፤ አባቱን ወይም እናቱን የሚሳደብ ይሙት’ ብሎ ነበርና፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ሙሴ፥ አባትህንና እናትህን አክብር፤ አባቱን ወይም እናቱን የሚሳደብ ፈጽሞ ይሙት ብሎ ነበርና፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ሙሴ ‘አባትህንና እናትህን አክብር፤’ ደግሞም ‘አባቱን ወይም እናቱን የሰደበ ፈጽሞ ይሙት፤’ ብሎአልና።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ሙሴ፦ አባትህንና እናትህን አክብር፤ ደግሞ፦ አባቱን ወይም እናቱን የሰደበ ፈጽሞ ይሙት ብሎአልና።

参见章节 复制




ማርቆስ 7:10
9 交叉引用  

“አባትህንና እናትህን አክብር፤ ይህን ብታደርግ እኔ በምሰጥህ ምድር የረዥም ዘመን ዕድሜ ይኖርሃል።


“አባቱን ወይም እናቱን የሚሰድብ በሞት ይቀጣ።


አባቱን ወይም እናቱን የሚሰድብ ሕይወቱ በድቅድቅ ጨለማ ጊዜ እንደሚጠፋ መብራት ይሆናል።


በአባቱ የሚያፌዝና እናቱ በምታረጅበት ጊዜ የሚንቃት ሰው የሸለቆ ቊራዎች ዐይኖቹን ጐጥጒጠው ያወጡታል፤ ጆፌ አሞራዎችም ይበሉታል።


ማንኛውም ሰው አባቱን ወይም እናቱን ቢሰድብ ይገደል፤ አባቱንና ወይም እናቱን ስለ ሰደበ ሞት የተፈረደበት በራሱ በደል ነው።


እግዚአብሔር ‘አባትህንና እናትህን አክብር፤ በአባቱ ወይም በእናቱ ላይ የስድብ ቃል የተናገረ በሞት ይቀጣል’ ብሎ አዞአል።


ትእዛዞችን ታውቃለህ፤ እነርሱም ‘አትግደል፤ አታመንዝር፤ አትስረቅ፤ በሐሰት አትመስክር፤ አታታል፤ አባትህንና እናትህን አክብር፤’ የተባሉት ናቸው።”


“ ‘አባቱን ወይም እናቱን የሚያዋርድ የተረገመ ይሁን!’ “ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ” ይበሉ።


“ ‘እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ባዘዝኩህ መሠረት አባትህንና እናትህን አክብር፤ ይህን ብታደርግ ሁሉ ነገር ይሳካልሃል፤ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ በምሰጥህ ምድር የረዥም ዘመን ዕድሜ ይኖርሃል።


跟着我们:

广告


广告