Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ማርቆስ 6:39 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

39 ኢየሱስም ሕዝቡን በቡድን ከፋፍለው፥ በለመለመው መስክ ላይ እንዲያስቀምጡአቸው ደቀ መዛሙርቱን አዘዘ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

39 ከዚያም፣ ሕዝቡን በለመለመ ሣር ላይ በቡድን በቡድን እንዲያስቀምጡ አዘዛቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

39 ከዚያም፥ ሕዝቡን በለመለመ ሣር ላይ በቡድን በቡድን እንዲያስቀምጡ አዘዛቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

39 ሁሉንም በየክፍሉ በለመለመ ሣር ላይ እንዲያስቀምጡአቸው አዘዛቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

39 ሁሉንም በየክፍሉ በለመለመ ሣር ላይ እንዲያስቀምጡአቸው አዘዛቸው።

参见章节 复制




ማርቆስ 6:39
9 交叉引用  

በሰሎሞን ገበታ ላይ የሚቀርበውን የምግብ ዐይነት፥ የመኳንንቱን መኖሪያ አካባቢዎች፥ የቤተ መንግሥቱን ሠራተኞች የሥራ አደረጃጀት፥ የደንብ ልብሳቸውንም ዐይነት፥ በግብዣ ጊዜ የሚያገለግሉትን አሳላፊዎችና በቤተ መቅደስም የሚያቀርባቸውን መሥዋዕቶችን ሁሉ ተመለከተች፤ በዚህም ሁሉ የተሰማት አድናቆት ከጠበቀችው በላይ ነበር።


ከዚያ በኋላ፥ ኢየሱስ ሕዝቡ በመሬት ላይ እንዲቀመጡ አዘዘ፤


እርሱም “ስንት እንጀራ አላችሁ? እስቲ ሂዱና እዩ፤” አላቸው፤ አይተውም “አምስት እንጀራና ሁለት ዓሣ አለ፤” አሉት።


ስለዚህ ሕዝቡ በመቶና በኀምሳ ተከፋፍለው በቡድን ተቀመጡ።


የሰዎቹም ብዛት አምስት ሺህ ያኽል ነበር። ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን “ሰዎቹ በኀምሳ፥ በኀምሳ ተከፋፍለው እንዲቀመጡ አድርጉአቸው” አላቸው።


ኢየሱስም “ሰዎቹ እንዲቀመጡ አድርጉአቸው” አለ። በዚያ ቦታ ብዙ ሣር ነበረ፤ ሰዎቹም ተቀመጡ፤ ቊጥራቸውም አምስት ሺህ የሚያኽል ነበር።


በእግዚአብሔር ሕዝብ አብያተ ክርስቲያን ሁሉ ዘንድ እንደሚደረገው እግዚአብሔር የሰላም አምላክ ነው እንጂ የሁከት አምላክ አይደለም።


ነገር ግን ሁሉ ነገር በአግባብና በሥነ ሥርዓት ይሁን።


跟着我们:

广告


广告