Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ማርቆስ 4:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ይህም የሚሆነው፥ ‘እነርሱ ወደ እግዚአብሔር ተመልሰው ኃጢአታቸው ይቅር እንዳይባልላቸው፥ ማየትን እያዩ ልብ አያደርጉም፤ መስማትን እየሰሙ አያስተውሉም፤’ ” በተባለው መሠረት ነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ይኸውም፣ “ ‘ማየቱን እንዲያዩ እንዳያስተውሉትም፣ መስማቱን እንዲሰሙ ልብ እንዳይሉትም፣ እንዳይመለሱና ኀጢአታቸው እንዳይሰረይላቸው ነው’ አላቸው።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ይኸውም፦ ተመልሰው ይቅር እንዳይላቸው፥ ‘ማየትን እያዩ ልብ አያደርጉም፤ መስማትን እየሰሙ አያስተውሉም፤’” አላቸው።

参见章节 复制




ማርቆስ 4:12
18 交叉引用  

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ዐይን እያላቸው የማያዩ ጆሮ እያላቸው የማይሰሙ፥ ሕዝቤን በአንድነት ሰብስቡ!


እንደዚህ ያሉት ሰዎች ዐይኖቻቸው ስለ ተሸፈኑ ማየት አይችሉም።


የይሁዳ ሕዝብ በእነርሱ ላይ ላመጣ ያቀድኩትን ጥፋት በሚሰሙበት ጊዜ ምናልባት ከክፉ ሥራቸው ይመለሱ ይሆናል፤ እኔም በደላቸውንና ኃጢአታቸውን ይቅር እላለሁ።”


እናንተ ዐይን እያላችሁ የማታዩ፥ ጆሮም እያላችሁ የማትሰሙ፥ እናንተ ሞኞችና ሰነፎች የሆናችሁ ሕዝብ ሆይ! ይህን ስሙ፤


“የሰው ልጅ ሆይ! አንተ የምትኖረው ዐመፀኞች በሆኑ ሕዝብ መካከል ነው፤ እነርሱ ዐመፀኞች ከመሆናቸው የተነሣ ዐይን እያላቸው አያዩም፤ ጆሮም እያላቸው አይሰሙም።


ዐይን እያላችሁ አታዩምን? ጆሮስ እያላችሁ አትሰሙምን? እንዴትስ ትዝ አይላችሁም?


ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “ለእናንተ የእግዚአብሔርን መንግሥት ምሥጢር ማወቅ ተሰጥቶአችኋል፤ ሌሎች ግን ሁሉ ነገር በምሳሌ ይነገራቸዋል፤ እነርሱ እያዩ ልብ እንዳያደርጉ፥ እየሰሙም እንዳያስተውሉ ነው።”


እንግዲህ ኃጢአታችሁ እንዲደመሰስላችሁ ንስሓ ገብታችሁ ወደ ጌታ ተመለሱ፤


እግዚአብሔር ግን እስከ ዛሬይቱ ዕለት ድረስ ያለፋችሁበትን ሁኔታ የምታዩበት ዐይን፥ የምትሰሙበት ጆሮ፥ የምታስተውሉበት አእምሮ አልሰጣችሁም።


እርሱ የሚቃወሙትን ሰዎች በገርነት የሚያርም መሆን አለበት፤ ምናልባትም እውነትን ያውቁ ዘንድ እግዚአብሔር ንስሓ የመግባትን ዕድል ይሰጣቸው ይሆናል።


ከዚህ ሁሉ በኋላ እምነታቸውን ቢክዱ እነርሱ ለራሳቸው የእግዚአብሔርን ልጅ እንደገና ስለሚሰቅሉትና በይፋ ስለሚያዋርዱት እነርሱን ወደ ንስሓ መመለስ አይቻልም።


跟着我们:

广告


广告