Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ማርቆስ 15:39 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

39 በመስቀሉ ፊት ለፊት ቆሞ የነበረ የመቶ አለቃ ኢየሱስ እንዴት ነፍሱ ከሥጋው እንደ ተለየች ባየ ጊዜ፥ “ይህ ሰው በእርግጥ የእግዚአብሔር ልጅ ነበር፤” አለ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

39 በኢየሱስ ትይዩ ቆሞ የነበረውም የመቶ አለቃ እንደዚህ ጮኾ ነፍሱን ሲሰጥ ባየ ጊዜ፣ “ይህ ሰው በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነበር!” አለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

39 በኢየሱስ ትይዩ ቆሞ የነበረውም የመቶ አለቃ እንደዚህ ጮኾ ነፍሱን ሲሰጥ ባየ ጊዜ፥ “ይህ ሰው በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነበር” አለ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

39 በዚያም በአንጻሩ የቆመ የመቶ አለቃ እንደዚህ ጮኾ ነፍሱን እንደ ሰጠ ባየ ጊዜ “ይህ ሰው በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነበረ፤” አለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

39 በዚያም በአንጻሩ የቆመ የመቶ አለቃ እንደዚህ ጮኾ ነፍሱን እንደ ሰጠ ባየ ጊዜ፦ ይህ ሰው በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነበረ አለ።

参见章节 复制




ማርቆስ 15:39
8 交叉引用  

እርሱ በእግዚአብሔር ታምኖአል፤ ‘የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ’ ብሎአል፤ ስለዚህ እግዚአብሔር የሚወደው ከሆነ እስቲ አሁን ያድነው!”


የመቶ አለቃውና ከእርሱም ጋር ኢየሱስን ይጠብቁ የነበሩት የምድርን መናወጥና የሆነውንም ነገር ባዩ ጊዜ እጅግ ፈርተው “በእውነት ይህ የእግዚአብሔር ልጅ ነበረ!” አሉ።


በቂሳርያ የሚኖር ቆርኔሌዎስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፤ እርሱም በሮማውያን ጦር ሠራዊት ሥር “የኢጣልያ ብርጌድ” በሚባለው ውስጥ የመቶ አለቃ ነበር።


የመቶ አለቃው ግን ጳውሎስን ለማዳን ስለ ፈለገ አሳባቸውን አልተቀበለም፤ ይልቁንም መዋኘት የሚችሉ አስቀድመው ከመርከቡ ወደ ባሕር እየዘለሉ ወደ ምድር እንዲወጡ አዘዘ።


跟着我们:

广告


广告