Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ማርቆስ 14:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 ጴጥሮስ ግን “መሞት እንኳ ቢያስፈልግ ከአንተ ጋር እሞታለሁ እንጂ ከቶ አልክድህም!” እያለ አጠንክሮ ተናገረ። የቀሩትም ደቀ መዛሙርት እንዲሁ ይሉ ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 ጴጥሮስም፣ “ከአንተ ጋራ ብሞት እንኳ ከቶ አልክድህም” በማለት ይበልጥ አጽንቶ ተናገረ። ሁሉም ደግሞ እንደዚሁ አሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 ጴጥሮስም፥ “ከአንተ ጋር ብሞት እንኳ ከቶ አልክድህም” በማለት ይበልጥ አጽንቶ ተናገረ። ሁሉም ደግሞ እንደዚሁ አሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 እርሱም ቃሉን አበርትቶ “ከአንተ ጋር የምሞት እንኳ ቢሆን ከቶ አልክድህም፤” አለ። ሁሉም ደግሞ እንደዚሁ አሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 እርሱም ቃሉን አበርትቶ፦ ከአንተ ጋር የምሞት እንኳ ቢሆን ከቶ አልክድህም አለ። ሁሉም ደግሞ እንደዚሁ አሉ።

参见章节 复制




ማርቆስ 14:31
17 交叉引用  

ንጉሡም “ስለምን ትሄዳለህ? ወደ አገርህ ለመሄድ ያሰብከው ከቶ ምን ተጓድሎብህ ነው?” አለው። ሀዳድም “ምንም የተጓደለብኝ ነገር የለም፤ ብቻ ወደ ትውልድ አገሬ እንድመለስ ፍቀድልኝ” ሲል ለንጉሡ መለሰ፤


አዛሄልም “እኔ ለምንም የማልጠቅም ኢምንት ነኝ! ታዲያ ይህን ሁሉ ለማድረግ የሚያስችለውን ኀይል ከቶ ከየት አገኛለሁ?” ሲል ጠየቀ። ኤልሳዕም “አንተ የሶርያ ንጉሥ እንደምትሆን እግዚአብሔር ገልጦልኛል” ሲል መለሰለት።


ዋስትና እንዳለኝ ስላወቅሁ “ከቶ አልሸነፍም” አልኩ።


ከዚህም በኋላ ሁሉም በአንድ ድምፅ ተባብረው “እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ እንፈጽማለን” አሉ፤ ሙሴም ይህንኑ ለእግዚአብሔር አቀረበ።


ትዕቢት ወደ ጥፋት ይወስዳል፤ ትምክሕተኛነትም ወደ ውድቀት ያደርሳል።


ወዳጆች ሳይሆኑ ወዳጆች መስለው የሚታዩ አሉ፤ እውነተኛ ወዳጅ ግን ከወንድም ይበልጣል።


ትምክሕተኛነት ወደ ውድቀት ያደርስሃል፤ ትሑት ከሆንክ ግን ትከበራለህ።


እግዚአብሔር ሆይ! ሰው በራሱ ሕይወት እንደማያዝበትና አካሄዱንም በራሱ ሥልጣን መቈጣጠር እንደማይችል ዐውቃለሁ።


“የሰው ልብ ከሁሉ ነገር በላይ ተንኰለኛና ጠማማ ነው፤ ውስጠ ምሥጢሩን የሚረዳ ማነው?


በሰው ፊት የሚክደኝን ሁሉ ግን እኔም በሰማይ አባቴ ፊት እክደዋለሁ።


እነርሱም “አዎ፥ እንችላለን፤” አሉ። ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “በእርግጥ እኔ የምጠጣውን ጽዋ ትጠጣላችሁ፤ እኔም የምጠመቀውን ጥምቀት ትጠመቃላችሁ፤


ኢየሱስም “በእውነት እልሃለሁ፤ ዛሬ በዚህች ሌሊት ዶሮ ሁለት ጊዜ ከመጮኹ በፊት አንተ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ፤” አለው።


ከዚህም በኋላ ጌቴሴማኒ ወደሚባል ስፍራ ሄዱ፤ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን፦ “እኔ እዚያ ስጸልይ እናንተ እዚህ ቈዩ፤” አላቸው።


እነርሱ ግን ድምፃቸውን ከፍ አድርገው “ስቀለው!” እያሉ ጮኹ፤ የሕዝቡና የካህናት አለቆች ድምፅ አየለ።


ጴጥሮስም “ጌታ ሆይ! ስለምን አሁን ልከተልህ አልችልም? እኔ ሕይወቴን እንኳ ስለ አንተ አሳልፌ እሰጣለሁ” አለው።


跟着我们:

广告


广告