Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ማርቆስ 12:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ከፈሪሳውያንና ከሄሮድስ ወገን የሆኑ አንዳንድ ሰዎች ኢየሱስን በንግግሩ ለማጥመድ ወደ እርሱ ተላኩ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ከዚያም በነገር እንዲያጠምዱት ከፈሪሳውያንና ከሄሮድስ ወገን ሰዎች ወደ እርሱ ላኩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ከዚያም በነገር እንዲያጠምዱት ከፈሪሳውያንና ከሄሮድስ ወገን ሰዎች ወደ እርሱ ላኩ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 በንግግርም ሊያጠምዱት ከፈሪሳውያንና ከሄሮድስ ወገን የሆኑትን ወደ እርሱ ላኩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 በንግግርም ሊያጠምዱት ከፈሪሳውያንና ከሄሮድስ ወገን የሆኑትን ወደ እርሱ ላኩ።

参见章节 复制




ማርቆስ 12:13
12 交叉引用  

ትምክሕተኞች ወጥመድ ዘረጉብኝ፥ እንደ መረብ የተጠላለፈ ገመድም ዘረጉብኝ። እኔንም ለመያዝ በመንገዴ ላይ ወጥመድ አጠመዱ።


ሊገድሉኝ የሚፈልጉ ወጥመድ ይዘረጉብኛል፤ ሊጐዱኝ የሚያቅዱ ሊያጠፉኝ ይዝታሉ፤ በእኔም ላይ ቀኑን ሙሉ ያሤራሉ።


ሰውን በነገር ወንጀለኛ የሚያደርጉ፥ ተከሳሽንም በፍርድ ሸንጎ የሚያጠምዱ፥ በሐሰተኛ ምስክር ንጹሕ ሰው ፍትሕ እንዳያገኝ በሐሰት የሚመሰክሩትን ሁሉ እግዚአብሔር ያጠፋቸዋል።


ከሕዝቡ መካከል አንዳንድ ሰዎች፦ “ኑ በኤርምያስ ላይ ዕቅድ እናውጣ! የእግዚአብሔርን ሕግ የሚያስተምሩ ካህናት፥ ምክር የሚሰጡ ጥበበኞች፥ የእግዚአብሔርን መልእክት የሚናገሩ ነቢያት ሁልጊዜ እናገኛለን፤ ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲያ ኤርምያስን ከማድመጥ ይልቅ በንግግሩ አጥምደን በወንጀል እንክሰሰው ተባባሉ።”


ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን “ልብ አድርጉ፤ ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን እርሾ ተጠንቀቁ” አላቸው።


ቀርበውም እንዲህ አሉት፤ “መምህር ሆይ፥ አንተ እውነተኛ መሆንህን እናውቃለን፤ ሰውንም በመፍራትና በይሉኝታ የምታደርገው ነገር የለም፤ የእግዚአብሔርንም መንገድ በእውነት ታስተምራለህ፤ ታዲያ፥ ለሮም ንጉሠ ነገሥት ግብር መክፈል ሕጋዊ ነውን? ወይስ አይደለም? እንገብር ወይስ አንገብር?”


ወዲያውኑ ፈሪሳውያን ወጥተው እንዴት አድርገው ኢየሱስን እንደሚያጠፉት ከሄሮድስ ሰዎች ጋር ተማከሩ።


ኢየሱስም “ከፈሪሳውያንና ከሄሮድስ እርሾ ተጠንቀቁ፤” ብሎ አዘዛቸው።


ይህንንም ያደረጉት በንግግሩ ሊያጠምዱት ፈልገው ነው።


跟着我们:

广告


广告