Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ማርቆስ 12:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ለመሆኑ፥ ‘ግንበኞች የናቁት ድንጋይ የማእዘን ራስ ሆነ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 እንዲህ የሚለውን የመጽሐፍ ቃል አላነበባችሁምን? “ ‘ግንበኞች የናቁት ድንጋይ፣ እርሱ የማእዘን ራስ ሆነ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ግንበኞች የናቁት ድንጋይ፥ እርሱ የማእዘን ራስ ሆነ፤ የሚለውን የመጽሐፍ ቃል አላነበባችሁምን፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10-11 ‘ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ ሆነ፤ ይህም ከጌታ ዘንድ ሆነ፤ ለዐይኖቻችንም ድንቅ ነው።’ የሚለውን ይህን መጽሐፍ አላነበባችሁምን?”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10-11 ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ ሆነ፤ ይህም ከጌታ ዘንድ ሆነ፥ ለዓይኖቻችንም ድንቅ ነው። የሚለውን ይህን መጽሐፍ አላነበባችሁምን?

参见章节 复制




ማርቆስ 12:10
17 交叉引用  

ስለዚህም ጌታ እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፦ “እነሆ፥ የጸና የመሠረት ድንጋይ በጽዮን አኖራለሁ፤ እርሱም የተመሰከረለት፥ የከበረ የማእዘን ድንጋይ ነው፤ በእርሱም የሚያምን ሁሉ አይናወጥም።


ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “ዳዊትና አብረውት የነበሩት ሰዎች በተራቡ ጊዜ ዳዊት ያደረገውን ከቶ አላነበባችሁምን?


ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እግዚአብሔር በመጀመሪያ ወንድና ሴት አድርጎ እንደ ፈጠራቸው አላነበባችሁምን?


ስለዚህ ኢየሱስን “እነዚህ ሕፃናት የሚሉትን ትሰማለህን?” አሉት፤ እርሱም “አዎ፥ እሰማለሁ፤ ‘ከልጆችና ከሚጠቡት ሕፃናት አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ’ የሚለውን ከቶ አላነበባችሁምን?” አላቸው፤


ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ “በቅዱሳት መጻሕፍት ‘ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ ዋና የማእዘን ራስ ሆነ፤ ይህም የጌታ ሥራ ነው፤ ለዐይኖቻችንም ድንቅ ነው፤’ ተብሎ የተጻፈውን ከቶ አላነበባችሁምን?


ደግሞ ስለ ሙታን መነሣት እግዚአብሔር ለእናንተ የነገራችሁን አላነበባችሁምን?


ስለ ሙታን መነሣት የሆነ እንደ ሆነ ግን እግዚአብሔር ሙሴን ከቊጥቋጦው እሳት ውስጥ ምን እንደ ተናገረው ከሙሴ መጽሐፍ አላነበባችሁምን? ይኸውም ‘እኔ የአብርሃም አምላክ፥ የይስሐቅ አምላክ፥ የያዕቆብ አምላክ ነኝ፤’ ያለው ነው።


“እንግዲህ የወይኑ ተክል ጌታ ምን ያደርጋል? ባለቤቱ ራሱ ይመጣል፤ ገበሬዎቹንም ይገድላል፤ የወይኑንም ተክል ለሌሎች ይሰጣል።


“ደግሞ መገኘት በማይገባው ስፍራ የሚያረክሰውን አጸያፊ ነገር ታያላችሁ፤ ይህንንም አንባቢው ያስተውል፤ በዚያን ጊዜ በይሁዳ ምድር ያሉ ወደ ተራራዎች ይሽሹ።


ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “ዳዊት ከተከታዮቹ ጋር በተራበና በተቸገረ ጊዜ ምን እንዳደረገ አላነበባችሁምን?


ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “እርሱና አብረውት የነበሩት ሰዎች በተራቡ ጊዜ ዳዊት ያደረገውን አላነበባችሁምን?


ይህም፦ “እነሆ፥ ሰዎችን የሚያሰናክል ድንጋይ በጽዮን አኖራለሁ፤ ይህም ድንጋይ ሰዎችን በማሰናከል የሚጥል አለት ነው፤ በእርሱ የሚያምን ግን አያፍርም” ተብሎ እንደ ተጻፈው ነው።


跟着我们:

广告


广告