Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ማርቆስ 10:29 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “በእውነት እላችኋለሁ፤ ስለ እኔና ስለ ወንጌል ብሎ ቤትን ወይም ወንድሞችን ወይም እኅቶችን ወይም እናትን ወይም አባትን ወይም ልጆችን ወይም ርስትን የሚተው ሰው ይበልጥ ያገኛል፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለ፤ “እውነት እላችኋለሁ፤ ስለ እኔና ስለ ወንጌል ሲል ቤትን ወይም ወንድሞችን ወይም እኅቶችን ወይም እናትን ወይም አባትን ወይም ልጆችን ወይም ዕርሻን የተወ ሁሉ፣

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለ፤ “እውነት እላችኋለሁ፤ ስለ እኔና ስለ ወንጌል ሲል ቤቱን ወይም ወንድሞቹን ወይም እኅቶቹን ወይም እናቱን ወይም አባቱን ወይም ልጆቹን ወይም ዕርሻውን የተወ ሁሉ፥

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለ “እውነት እላችኋለሁ፤ ስለ እኔና ስለ ወንጌል ቤትን ወይም ወንድሞችን ወይም እኅቶችን ወይም አባትን ወይም እናትን ወይም ሚስትን ወይም ልጆችን ወይም እርሻን የተወ፥

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ ስለ እኔና ስለ ወንጌል ቤትን ወይም ወንድሞችን ወይም እኅቶችን ወይም አባትን ወይም እናትን ወይም ሚስትን ወይም ልጆችን ወይም እርሻን የተወ፥

参见章节 复制




ማርቆስ 10:29
13 交叉引用  

በግብጽ ምድር ለም የሆነውን ቦታ ስለሚያገኙ ቤት ንብረታቸውን ትተው በመምጣታቸው ቅር አይሰኙ።”


በእኔ ምክንያት፥ ወደ ገዢዎችና ወደ ነገሥታት ለፍርድ ስለምትወሰዱ በእነርሱና በአሕዛብ ፊት ምስክሮቼ ትሆናላችሁ፤


ስለ እኔ ብሎ ቤቶችን፥ ወይም ወንድሞችን፥ ወይም እኅቶችን፥ ወይም አባትን ወይም እናትን፥ ወይም ልጆችን፥ ወይም እርሻን የተወ ሁሉ መቶ እጥፍ ይቀበላል፤ የዘለዓለም ሕይወትንም ያገኛል።


እናንተ ግን፥ አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥትና ጽድቁን ፈልጉ፤ የቀረው ነገር ሁሉ ይጨመርላችኋል፤


ሕይወቱን ለማዳን የሚፈልግ ሁሉ ያጣታል፤ ስለ እኔና ስለ ወንጌል ሕይወቱን አሳልፎ የሚሰጥ ግን ያድናታል፤


ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “በእውነት እላችኋለሁ፤ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ብሎ ቤቱን ወይም ሚስቱን ወይም ወንድሞቹን ወይም ወላጆቹን ወይም ልጆቹን የሚተው ሰው፥


ይህን ሁሉ ማድረጌ የወንጌልን በረከት ለመካፈል ስለ ወንጌል ብዬ ነው።


በትዕግሥት መጽናትህንና ስለ ስሜም ሳትሰለች መከራ መቀበልህን ዐውቃለሁ፤


跟着我们:

广告


广告