Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሚልክያስ 1:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 እናንተም ይህን ሁሉ በዐይናችሁ አይታችሁ “እግዚአብሔር ከእስራኤል ምድር ውጪ እንኳ ኀያል ነው!” ትላላችሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ይህንም በገዛ ዐይናችሁ ታያላችሁ፤ እናንተም፣ ‘ከእስራኤል ዳርቻ ወዲያ እንኳ እግዚአብሔር ታላቅ ነው!’ ትላላችሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ዐይኖቻችሁም ያያሉ፥ እናንተም፦ “ከእስራኤል ዳርቻ ወዲያ ጌታ ታላቅ ይሁን!” ትላላችሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ዓይኖቻችሁም ያያሉ፥ እናንተም፦ እግዚአብሔር ከእስራኤል ዳርቻ ወዲያ ታላቅ ይሁን ትላላችሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ዓይኖቻችሁም ያያሉ፥ እናንተም፦ እግዚአብሔር ከእስራኤል ዳርቻ ወዲያ ታላቅ ይሁን ትላላችሁ።

参见章节 复制




ሚልክያስ 1:5
14 交叉引用  

በዚህም ምክንያት የእግዚአብሔር ቊጣ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ ወረደ፤ እናንተም እንደምታዩት በእነርሱ ላይ ፍርሀትንና ድንጋጤን አምጥቶባቸዋል፤ መዘባበቻም አድርጎአቸዋል።


በሕዝቤ በእስራኤል ላይ ምድርን እንደሚሸፍን ደመና ትመጣባቸዋለህ፤ ጎግ ሆይ፥ በኋለኛው ዘመን በምድሬ ላይ እንድትመጣ አደርግሃለሁ፤ ይህንንም የማደርገው በአንተ አማካይነት ቅድስናዬን በፊታቸው በምገልጥበት ጊዜ ሕዝቦች እንዲያውቁኝ ነው።’ ”


በዚህም ዐይነት ታላቅነቴንና ቅድስናዬን አሳያለሁ፤ በብዙ ሕዝቦችም ዘንድ ራሴን አሳውቃለሁ፤ ከዚያ በኋላ እነርሱ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃሉ።”


በእስራኤል ከተሞች የሚኖሩ ሕዝብ ወጥተው የተጣለውን የጦር መሣሪያ ሁሉ ለእሳት ማገዶ እንዲሆን ይሰበስባሉ፤ ጋሻውን፥ ቀስቱን፥ ፍላጻውን፥ ጦሩንና ዱላውን ሁሉ ሰብስበው ያነዱታል፤ ለሰባት ዓመት የሚበቃም ማገዶ ይኖራቸዋል።


እርሱ በእግዚአብሔር ኀይል ተነሥቶ የበግ መንጋውን ያሰማራል፤ ይህንንም የሚያደርገው በግርማዊው በእግዚአብሔር በአምላኩ ስም ነው፤ እርሱ አሁን እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ታላቅ ስለሚሆን እነርሱ ያለ ስጋት ይኖራሉ።


እግዚአብሔር ያደረጋቸውን እነዚህን ታላላቅ ነገሮች ሁሉ በዐይናችሁ ያያችሁ እናንተ ራሳችሁ ናችሁ።


በፔዖር ተራራ ላይ እግዚአብሔር ያደረገውን ሁሉ ራሳችሁ በዐይናችሁ አይታችኋል፤ ይኸውም በዚያ ተራራ ላይ ባዓል ተብሎ ለሚጠራው ጣዖት የሚሰግዱትን ሁሉ ደምስሶአል፤


እረዳቸው ዘንድ ወደ እኔ ጮኹ፤ እኔም በእነርሱና በግብጻውያን መካከል ጨለማ እንዲሆን አደረግሁ። ባሕሩም እንዲከነበልባቸው አድርጌ ግብጻውያንን አሰጠምሁ፤ በግብጻውያን ላይ ምን እንዳደረግሁ በዐይኖቻችሁ አይታችኋል፤ ከዚያም በኋላ እናንተ ለብዙ ጊዜ በበረሓ ኖራችሁ።


ስለዚህ ባላችሁበት ጸንታችሁ ቁሙ፤ እግዚአብሔር በፊታችሁ የሚያደርገውንም ድንቅ ነገር ታያላችሁ፤


跟着我们:

广告


广告