Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሚልክያስ 1:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 እግዚአብሔር በነቢዩ በሚልክያስ አማካይነት ለእስራኤል ሕዝብ የተናገረው የትንቢት ቃል ይህ ነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 በሚልክያስ በኩል ወደ እስራኤል የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ንግር ይህ ነው፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 በሚልክያስ እጅ ለእስራኤል የሆነ የጌታ ቃል ይህ ነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 በሚልክያስ እጅ ለእስራኤል የሆነ የእግዚአብሔር ቃል ሸክም ይህ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 በሚልክያስ እጅ ለእስራኤል የሆነ የእግዚአብሔር ቃል ሸክም ይህ ነው።

参见章节 复制




ሚልክያስ 1:1
9 交叉引用  

የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ እግዚአብሔር ገልጦለት ስለ ባቢሎን የተናገረው የትንቢት ቃል ይህ ነው፤


እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፥ “ኤርምያስ ሆይ! ነቢይ ወይም ካህን ወይም ከሕዝቤ አንዱ፥ ‘የእግዚአብሔር ሸክም ምንድን ነው?’ ብሎ ቢጠይቅህ፥ ‘የእግዚአብሔር ሸክም እናንተ ናችሁ፤ ስለ ሆነም ከፊቱ ያስወግዳችኋል’ ብለህ ንገራቸው።


ስለ ነነዌ ጥፋት ኤልቆሻዊው ናሆም የተናገረው ቃልና ያየው ራእይ የሚከተለው ነው።


እግዚአብሔር ለነቢዩ ለዕንባቆም በራእይ የገለጠለት ቃል የሚከተለው ነው፦


ዳርዮስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት፥ ስድስተኛው ወር በገባ በመጀመሪያው ቀን፥ እግዚአብሔር በነቢዩ አማካይነት በሐጌ ተናገረ የተናገረውም የይሁዳ ገዢ ለነበረው ለሰላትያል ልጅ ለዘሩባቤልና ሊቀ ካህናት ለነበረው ለኢዮሴዴቅ ልጅ ለኢያሱ ነው።


ዳርዮስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት፥ ሰባተኛው ወር በገባ በሃያ አንደኛው ቀን በነቢዩ ሐጌ አማካይነት እግዚአብሔር ዳግመኛ ተናገረ፤


ሰማይን የዘረጋ፥ ምድርን የመሠረተ፥ ለሰውም የሕይወትን እስትንፋስ የሰጠ እግዚአብሔር ስለ እስራኤል እንዲህ ይላል፦


የሰዎችና የእስራኤል ነገዶች ዐይኖች ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ይመለከታሉ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር በሐድራክና በደማስቆ ከተሞች ላይ ይፈርዳል።


የይሁዳ ሕዝብ እምነተቢስ ሆኖአል፤ በእስራኤልና በኢየሩሳሌም አጸያፊ የርኲሰት ሥራ ፈጽመዋል፤ ይህም የሆነው ጣዖት አምላኪዎች የሆኑ የባዕድ ሴቶችን በማግባት ይሁዳ እግዚአብሔር የሚወደውን ቤተ መቅደስ ስላረከሰ ነው።


跟着我们:

广告


广告