Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሉቃስ 21:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ይህ ሁሉ መሆን በሚጀምርበት ጊዜ መዳናችሁ ቀርቦአልና ቀና ብላችሁ ወደ ላይ ተመልከቱ።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 እናንተም እነዚህ ነገሮች መፈጸም ሲጀምሩ፣ መዳናችሁ ስለ ተቃረበ ቀጥ ብላችሁ ቁሙ፤ ራሳችሁንም ወደ ላይ ቀና አድርጉ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 ይህም መሆን ሲጀምር መዳናችሁ ቀርቦአልና ቁሙ፤ ቀናም በሉ።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 ይህም ሁሉ በሆነ ጊዜ ወደ ላይ አቅ​ን​ታ​ችሁ ተመ​ል​ከቱ፤ ራሳ​ች​ሁ​ንም አንሡ፤ የሚ​ያ​ድ​ና​ችሁ መጥ​ቶ​አ​ልና።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 ይህም ሊሆን ሲጀምር ቤዛችሁ ቀቦአልና አሻቅባችሁ ራሳችሁን አንሡ።

参见章节 复制




ሉቃስ 21:28
11 交叉引用  

ከዚያም ከዐሥራ ስምንት ዓመት ጀምሮ ርኩስ መንፈስ ጀርባዋን ያጐበጣት አንዲት ሴት ነበረች፤ እርስዋ ወገብዋ በመጒበጡ ቀና ለማለት በፍጹም አትችልም ነበር።


እግዚአብሔር ታዲያ፥ ሌት ተቀን እየጮኹ ለሚለምኑት ሕዝቦቹ አይፈርድላቸውምን? ችላ በማለትስ ርዳታውን ያዘገይባቸዋልን?


ቀጥሎም ኢየሱስ ይህን ምሳሌ ነገራቸው፦ “የበለስን ዛፍና የሌሎችንም ዛፎች ሁኔታ ልብ ብላችሁ ተመልከቱ፤


ፍጥረት ሁሉ የእግዚአብሔርን ልጆች መገለጥ በታላቅ ናፍቆት ይጠባበቃል።


ነገር ግን በመቃተት ላይ ያለው ፍጥረት ብቻ አይደለም፤ የመጀመሪያውን የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ የተቀበልን እኛም የሰውነታችን ቤዛ የሆነውን የእግዚአብሔር ልጆች መሆንን በተስፋ እየተጠባበቅን በውስጣዊ ሰውነታችን በመቃተት ላይ እንገኛለን፤


ይህ መንፈስ ለክብሩ ምስጋና እንዲሆን እግዚአብሔር የራሱ የሆኑትን በሙሉ እስኪዋጅ ድረስ ልናገኝ ላለው ርስታችን መያዣችን ነው።


ለምትዋጁበት ቀን ማረጋገጫ እንዲሆናችሁ የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔር መንፈስ አታሳዝኑ።


跟着我们:

广告


广告